Ethio Readers.com
የኢትዮጵያ ደራስያን በፊደል ማውጫ
 
Members Login
Your Email/Username
Password:
 

New member? Sign up!

Forgot password?

 
ጦማር
 
የልብ ወለድ ሥነጽሑፍ ጉዞ
ሥነ ጽሑፍ ጠቅላላ ዓላማው ማስደሰት ነው። ይህንንም ጉልህ አላማ የሚፈጽመው ሁሉን አቀፍ የሕይወት ኂስ በማቅረብ ነው። ሥነ ጽሑፍ ጉልህ ዓላማውን ለመፈጸም ጥራትና ወጥነት እንዲኖረው ያስፈልጋል።" በኑኀ ዘመን ፥ በቀን ብዛት የማይነቅዝና የማይሻግት" መሆን አለበት። አለበለዚያ አጉል ጒህና ወይም ብስና እንጂ ሥነ ጽሑፍ ሊሆን አይችልም።
ዶ/ር እጓለ ገብረዮሐንስ፤ በ‹‹ የሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ የመጀመሪያ የሥዕል ትርኢት ካታሎግ ፲፱፻፶፮ ዓ.ም ›› ላይ ያቀረቡት የመግቢያ ጽሑፍ።
ይህ ደራሲ እንደሚለው ሰው ከሌሎቹ ሕያዋን የሚለይበት ዋናው ምልክት ጥበብ የምንለው ነው። የተሳሳተ አይመስለኝም። ፈረንጆችን የጥበብን ባሕርይ በሚገባ ስለሚረዱ ሌላ መግለጫ ዘዴ ቢያጡ የጥበበኛውን የሥራ ጠባይ ከፈጣሪነት ጋር አስተካክለው ይናገራሉ። በሀገራችን የሐሳብ ዘዴ ፈጣሪነት ከመለኮት ጋር ብቻ የተያያዘ ነው።
‹‹የጠፈር ባይተዋሩ›› ሠዓሊና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታ ክፍል አንድ

ብርሃነ መስቀል ደጀኔ

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነጥበብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሥፍራ የነበረው ሠዓሊና ባለቅኔ ለማስታወስ ያህል ሠዓሊና ባለቅኔው ገብረክርስቶስ ደስታ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሥነጥበብ ህዋ ላይ በተለይ ‹‹አብስትራክት›› የተሰኘውን ዘመናዊ የሥዕል አሠራር ስልት


 

 

 
   
 
ሊነበቡ የሚገባቸው 10 ምርጥ የታሪክ መጻሕፍት
ሊነበቡ የሚገባቸው 10 ምርጥ ልቦለድ ድርሰቶች
ሊነበቡ የሚገባቸው 10 ምርጥ የግጥም መድብሎች
   

 

መጽሐፍ መፈለጊያ/Search Books
የሚፈልጉትን የአማርኛ ፊደል ለመጻፍ ከፊደሉ ፊት የተጻፈውን የንግሊዘኛ ፊደል ከኬይቦርድ ላይ ይጫኑ። X
 
 
 
 

በቅርቡ በገበያ ላይ የዋሉ አዳዲስ መጻሕፍት
"TOWER IN THE SKY by Hiwot Tefera " ማማ በሰማይ በሚል ርእስ ጌታነህ አንተነህ እንደተረጎመው።
ፍጹም ነው እምነቴ ቀይ ሽብር የከፍተኛ 15 እውነተኛ ታሪክ በነሲቡ ስብሓት።
ለደራሲው ስምንተኛ ስራው የሆነውና 600 ገጾች ያሉት “መረቅ”፣ በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች የተዋቀረ መጽሐፍ ነው።
...ሀገር ውስጥ የነበረው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ በተለይም የአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ገና ከምንጩ በዲሞክራሲያዊ ውይይትና መግባባት የሚያምን ህጋዊ ይፋዊ አብዮታዊ አመራርና በሃይል በአሸባሪነት ብቻ የሚያምን ህቡእ አመራር አቅፎ ነበር። ክፋቱ ሁለቱም አዝማሚያዎች በረዥም አብዮታዊ ትግል ሳይለያዩ የየካቲት አብዮት ስለፈነዳ፣ ሁለቱም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ በተለይም በኢህአፓ ውስጥ ተያይዘው በፖለቲካ መድረኩ ላይ ብቅ አሉ።
Wore Negari is the story of Mohamed Yimam and his friends in times of major social and political upheaval in Ethiopia.Through out the pages of the book Mohamed narrates the struggle with in himself to be a revolutionary like his peers. Sucked into a revolutionary current that he couldnt withstand. Mohamed flows with events of the seventies to a near disastrous end. In Wore Negari , he looks back and confronts his actions with unflinching honesty. This is a story of brave but misguided youth in their revolutionary fervor. Above all it is a human story of a family in distress , a country in turmoil, an individual at war within himself, and young people with extraordinary courage who throw everything they had to the cause they believed in.

ዘነበ ወላ የቀድሞውን ማስታወሻ መጽሐፉን በማስፋፋትና በማግዘፍ አፍቅሮትና አድናቆት ባልተለየው መልኩ የስብሐት ገብረ እግዚአብሄርን ሰብዕናና ስራዎቹን በዝርዝር በማቅረብ የአየር ንብረት የማይደፍረው ሐውልት አቁሞለታል ለማለት ይቻላል።
ገነነ መኩሪያ ኢሐፓና እስፖርት
የደ/ር ዮናስ አድማሱ የግጥም መድብል።
ደራሲው
የቀድሞው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ቪኦኤ ጋዜጠኛ ወርቅ አፈራሁ ከበደ በ1998 ዓ.ም. Borderless Love An Ethiopian-Eritrean Love በሚል ርእስ የመጀመሪያ መጽሐፉን በእንግሊዘኛ ቋንቋ አሳተመ። ይህ በእጅዎ የያዙት "ሤራ!በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት" የደራሲው ሁለተኛ መጽሐፍ ሲሆን፣የመጽሐፉ የመጀመሪያው ክፍል Volume I ነው። ወርቅ አፈራሁ ከSouthern Illinois University ሳውዘርን ኢሊዮን ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኛነት ትምህርት በማስተርስ ዲግሪ የተመረቀ ነው።
ከእንጦጦ እስከ ባሮ በምንሊክ ዘመነ መንግስት በሩሲያዊው እስክንድር ቡላቶቪች በሩሲያ ቋንቋ ተጽፎ በዶር. ኣምባቸው ከበደ ወደ አማርኛ የተመለሰ በጊዜው የነበረውን የደቡብ ኢትዮጵያ ምድራዊ አቀማመጥን ጨምሮ የሕዝቡን አኗኗር እንዲሁም ባሕልና እምነት የሚተርክ መጽሐፍ።
 
         

በቅርቡ በድጋሚ የታተሙ ቀደምት መጻሕፍት
ደራሲ ሐዲስ አለማየሁ የኖሩበትን የፊውዳሉን ዘመን ባህል፣ አስተሳሰብ እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ በዘመኑ ያልተፈጠረን አንባቢን ጭምር በምናቡ ዘመኑን እየሳለ ያልኖረበትን ዘመን ጣእም እንዲያጣጥም ያስቻለበት ድንቅ የፍቅር መጽሐፍ ነው። በኢትዮጵያ ዘመናዊ የአማርኛ የልቦለድ ስነጽሑፍ ታሪክ በብዙ ጸሐፍት ቁንጮ ስፍራን የያዘም ነው።
ከስብሃት የምንጊዜም ምርጥ ድርሰቶች እናትን እንዲሁም አምስት ስድስት ሰባት የተካተቱበት።
         

አንባብያን ቢያነቧቸው የሚመከሩ መጻሕፍት
የብላቴን ጌታ ፀጋዬ ገብረመድህን ምርጥ የግጥም ስብስብ የያዘ መድብል ነው።

ከመጽሐፉ የተወሰደ
"ፍቅርን ከድርሳናት የሚማሩቱ ቢኾን ሰሎሞን ለፍፅምት ሱላማጢስ ያወረደው ቅኔ: ያዜመው ስባሕታየ ስባሔ ለኹሉ በበቃ ነበር። ውነቱ ግን እንዲያ አይዶለም።"
ከመጽሐፉ የተወሰደ
“ሰው ሀብታም ሆነ ደሀ ልዩነቱ የሚታየው በዝቅተኛ የዕውቀት እና የእምነት ደረጃ እስካለ ድረስ ብቻ ነው። ወደ ላይ ከፍ ካሉ በኋላ ወደ ፍጹምነት ደረጃ ሲደርሱማ የሚያስቡለት የሚሰስቱለት ነገር አይሆንም። እዚህ ከፍታ ላይ ያለ ሰው ብዙ ቢኖረው አይተርፈውም። ስለሚያካፍል፤ ትንሽም ያለው አያንሰውም። ብዙ ስለማይፈልግ ነው። ወደዚህ ዓለም ይዞት የመጣው፣ ሲሔድም የሚያከትለው አንዳች ነገር አለመኖሩን ያውቃልና ነው”
ሀገር፣መንደር፣ቤት ንብረቱን ትቶ ወደ ሩቅ የሄደ ሰው ባይተዋር ይባላል። ይህ ስያሜ በኑሮ አድራሻ መለወጥ ብቻ ምክንያቱን የሚያገኝ አይደለም ።የመንፈስ ባይተዋርነትም አለ። ሰው ከነበረበት ቦታ ወደ ሌላ ሳይዘዋወርም ለአዲስ አስተሳተሰብ፣ ፈሊጥና የኑሮ መልክ ሊጋለጥ ይችላል።አንደኛው እስኪያይል ወይም ሁለቱም እስኪዋሐዱ ድረስ የወትሮው እና የአሁኑ በህሊና ውስጥ የባላንጣዎች ተቃርኖ ይፈጥራሉ። እንዲህ ያለ ሰውነት ሲታገል ይቆይና ሲሰለቸው የቸልተኝነት የግዴለሽነት ኢንዲፈረንቲዝም መንፈስ ይሰፍንበታል። ይህ በተለይ የሚገለጸው በሥነ ምግባር መስክ ነው። ሥለታም የነበረው ሥነ ምግባራዊ በሕሊናው ይሰንፋል። የሚመቹ፣ የማይቆረቁሩ፣ የማይጋጩ እንደ ዘዴኝነት፣ ጮሌነት፣ ብልሃተኝነት ያሉ የማይጨበጡ የቀልጣፋ ሰውነት ጠባዮች ያይላል። " አስመሳይ፤ አድር ባይ እንደ እምነቱ የማይኖር እንደ ኑሮው የማያምን የሕሊናውን ብኩርና ለምስር ንፍሮ የለወጠ" ሌላም ሌላም እንደ አለንጋ የሚጋረፉ ተግሣጾች ወቅታዊነታቸውን የሚያገኙት በዚህ ሳቢያ ይመስለናል። "የሞራል ድቀት" የሚባለው ይህ ሳይሆን ይቀራልን? የመነሳቱ፣ የመቆሙ ከራሱ ጋር ተስማምቶ ሚዛን ጠብቆ የመራመዱ ነገርስ እንዴት ይሆን? ቅን ሕሊና የማያልፈው ጥያቄ ነው።
የሃበሻ ጀብዱ የማይጨው ጦርነት ከዝግጅቱ እስከ መጨረሻ ፍልሚያው በነበሩ ኢትዮጵያን በግንባር ተገኝተው ይደግፉ በነበሩት ቼኮዝላቫኪያዊው አዶልፍ ፓርለሳክ የአይን እማኝነት የተጻፈ ነው ። የጦርነቱን አመጣጥና ዝግጅት እያስቃኘ የሃበሻን ወደር የለሽ ጀግንነት፣ አምላኩን ወዳጅ፣ ሀገሩንና ሃይማኖቱን አጥብቆ አክባሪ ታማኝ እና ለክብሩ ሟች እንደሆነ የሚመሰክር መጽሐፍ ነው።
         
         
በየመጻሕፍት መደብሮች የሚገኙ አዳዲስ መጻሕፍት /New Released Books
         
የዚህ ድረ-ገጽ መሠረታዊ ይዘቶች የተቃኙት በ
<< ያሠርቱ ምእት ፥ የብርእ ምርት ( ከ፲፻ እስከ ፳፻ ) ድርሰት ክፍል ፩
ጳጉሜን ፫ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ.ም በብርሃነመስቀል ደጀኔ 'ና
ጌታሁን ሽብሩ >>
በተዘጋጀው ያልታተመ ጥናታዊ ጽሑፍ ነው።
 
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2006 ዓ.ም ethioreaders.com