[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
የኢትዮጵያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
አ
በ
ቨ
ገ
ደ
ጀ
ሀ
ወ
ዘ
ዠ
ሐ
ኀ
ጠ
ጨ
የ
ከ
ኸ
ለ
መ
ነ
ኘ
ሠ
ዐ
ፈ
ጸ
ፀ
ቀ
ረ
ሰ
ሸ
ተ
ቸ
ጰ
ፐ
ወደ ዋና ገጽ
ሀብተማርያም ወርቅነህ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሀሰን አማኑ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሁሴን አሕመድ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1902 - 1996]
ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሐዲስ ዓለማየሁ በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረማርቆስ አውራጃ ከየኔታ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከወ/ሮ ደስታ ዓለሙ ጥቅምት 7 ቀን 1902 ዓ.ም. የተወለዱ ሲሆን፥ ለቤተሰባቸው ብቸኛ ልጅ ናቸው።
ሀዲስ እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ በቤተሰባቸው አጠገብ እና በአባታቸው ሀገር ደብረ ኤልያስ ሄደው ከባህላዊ የግዕዝ ት/ቤት ዜማ ተምረዋል፥ቅኔ ተቀኝተዋል።
በ1918 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ የመጡት ሀዲስ፥በዚያው አመት በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርታቸውን ተከታትለው በኢጣሊያ ወረራ ዋዜማ በአዲስ አበባ በመምህርነት በጎጃም በጉምሩክ ሥራ ባለሙያነት ሠርተዋለል።
በኢጣሊያ ወረራ ወቅት 1929-1933 ዓ.ም. ከልዑል ራስ አምኃ ኃ/ስላሴ ጦር ጋር በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በምእራብ ኢትዮዽያ በጣሊያን ተማርከው፥ ወደ ኢጣሊያ በግዞት ከቆዩ በኋላ በ1936 ዓ.ም. ወደ ሀገራቸው በነፃነት ተመልሰዋል።
ከነፃነት በኋላ ዘመናዊት ኢትዮዽያን ለማደራጀት በተደረገው ትግል በማስታወቂያ ሚኒስቴር 1936፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር - በኢየሩሳሌም 1937-1939 እና በተ.መ.ድ 1939-1946፥ በእንግሊዝ 1948፥ እንደገና በተ.መ.ድ 1949-1953 ሀገራቸውን በአምባሳደርነት ያገለገሉ ሲሆን በዚሁ "ወርቃማ" የሥራ ዘመናቸው በመዲናችን አዲስ አበባ- የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ECA እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደጉ ክቡር ኢትዮዽያዊ ናቸው።
ከ1953 ዓ.ም. የታኅሣሡ መፈንቅለ መነግስት ሙከራ በኋላ እስከ 1961 ዓ.ም. ድረስ በሚኒስትርነት ማእረግ በሚኒስትሮች ም/ቤት የመማክርት ጉባኤ አባል፥ ከ1961 - እስከ 1966 ድረስ በሀገሪቱ ፓርላማ የህግ መወሰኛ ም/ቤት አባል ከ1966 ጎጃም ሕዝብ በመረጣቸው መሰረት የብሄራዊ ሸንጎ አባል 1966-1968 ሆነው ያገለገሉ ሀዲስ ዓለማየሁ "ኢትዮዽያ ምን አይነት አስተዳደር ያስፈልጋታል?" 1966 በሚለው መጽሐፋቸው ስለ ሀገራቸው ያላቸውን የመልካም አስተዳደር ራእይ ተመልክቶ ደርግ የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ሆነው እንዲሰሩ ጠይቋቸው አለመቀበላቸው ተነግሯል።
ሀዲስ አለማየሁ በ1929 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ካዘጋጁዋት "ያበሻና የወደኋላ ጋብቻ" በኩር የተውኔት ድርሰታቸው ፋቡላ አንስቶ "ተረትተረት የመሰረት" 1948 "ፍቅር እስከመቃብር" 1958፥ ወንጀለኛው ዳኛ 1974፥ "የልምዣት" 1980 በተሰኙት የረዥም ልቦለድ ሥራዎቻቸው ያልታተሙ ድርሰቶችም አሏቸው የኢትዮዽያን ዘመናዊ ሥነጽሑፍ በአያሌው የታደጉ "የቀለም ሰው" ናቸው።
ሀዲስ ዓለማየሁ "ፍቅር እስከመቃብር" በተሰኘው የአማርኛ ረዥም ልቦለድ ሥራቸው "ለኢትዮዽያ ሥነጽሁፍ አዲስ ምእራፍ ከፋች!" የሚል ሞገስ ያገኙ ሲሆን፥ በዚሁ ኪናዊ ሥራቸውም ፋሽስት ኢጣሊያ ከወጣ በኋላ ብዚዎቹ ኢትዮዽያውያን ደራስያን ያላተኮሩበትን የፊውዳል ኢትዮዽያን ገፅታ በተለየ ትኩረት በስፋትና በጥልቀት በመዳሰስ ኪናዊ በሆነ የቋንቋ ኃይልና ውበት የገለጹ፥ በፊውዳሉ ሥርዓት ላይ ያመፁ እንደ ጉዱ ካሣ፥ በዛብህ፥ ሰብለወንጌል፥ አበጀን የመሳሰሉ ሕይዋን ገፀባሕርያት በመሳል - በለውጥ የትግል መንፈስ ላይ ለነበረው አዲስ ትውልድ ሀዲስ ራዕያቸውን በጥበብ አጋርተዋል።
በአጻጻፍ ብልሃቱ በአማርኛ ሥነ ጽሁፍ ታሪክ ውስጥ አዲስ ፈር በቀደደው የ"ፍቅር እስከ መቃብር" ድርሰታቸው በሁለት የውጭ ቋንቋዎች ተተርጉሟል "አዲስ ዓለም አሳየን!" የሚል ሞገስ ያገኙት ሀዲስ ዓለማየሁ በ1960 ዓ.ም የቀ.ኃ.ሥ. ሽልማት ክብር በሥነጽሁፍ ነሐሴ 27 ቀን 1991 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሑፍ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል።
"ትዝታ" 1985 በሚለው ግለ ታሪካቸው ሰብዕናቸውን የተረኩልን ታረክ ፀሐፊ፥ አርበኛ መምህር፥ አምባሳደር፥ ሚኒስትርና የሥነ ጽሑፍ ጠቢብ ሃዲስ ዓለማየሁ "የኢትዮዽያ ሥነ ጽሑፍ አባት!" የሚል የሀያስያንና የሕዝብ ሞገስ አግኝተው ኅዳር 28 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው አረፉ።
ምንጭ:
ብርሀነመስቀል ደጀኔ 2000ዓ.ም ብራና.ማ.ቤ ካሌንደር።
ሐዲስ ዓለማየሁ በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረማርቆስ አውራጃ ከየኔታ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከወ/ሮ ደስታ ዓለሙ ጥቅምት 7 ቀን 1902 ዓ.ም. የተወለዱ ሲሆን፥ ለቤተሰባቸው ብቸኛ ልጅ ናቸው።
አለቃ ሐረገ ወይን በየነ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሐዲስ ወልደ ጻድቅ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሐፊዝ ዳውድ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሐዋርያ ክርስቶስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሐሪ አትክንስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሐማ ቱማ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሕይወት ሕዳሩ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ሕይወት ተፈራ Hiwot teffera
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ኃይሉ ሻወል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ኃይሉ ሻወል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ራስ መኮንን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ደጃች ኃይሉ እሸቴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ኃይለሥላሴ፥መርስኤ ሐዘን ወል መላከ ገነት ክፍሌ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ገሞራው ኃይሉ ገብረዮሐንስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መኖር ሕልው ነው - በመንፈስ በአካል፣
ያላዩኝ ወገኖች ቢሉም ሞቷል አልፏል፣
ለሚፎክሩትም - ፀረ ሰብ ተንባላት!
ግልጡ አካሌ ይኸው ነፍሴን ግን አይገሏት!
።
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
መኖር ሕልው ነው - በመንፈስ በአካል፣
ያላዩኝ ወገኖች ቢሉም ሞቷል አልፏል፣
ለሚፎክሩትም - ፀረ ሰብ ተንባላት!
ግልጡ አካሌ ይኸው ነፍሴን ግን አይገሏት!
።
ኃይለመለኮት መዋዕል መሐሪ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ኃይለመለኮት መዋዕል ሰኔ ፩፮ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ ይፋት አውራጃ ማጀቴ ተወለዱ። በአማርኛ ትምህርት ደቡብ ኮምቦልቻ ፊደል ቆጥረው፣ ዳዊት ከደገሙ በኋላ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ የኤርትራ ክ/ሀገር አሥመራ ከተማ አክሪያ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም እንዲሁ በአሥመራ ልዑል መኮንን መታበቢያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡ በመምህርነት ሙያም ሠልጥነዋል፡፡
ኃይለመለኮት መዋዕል “የወዲያነሽ”፣ እና “ጉንጉን” በሚሉ ርዕሶች ሁለት መጻሕፍት ለንባብ አብቅተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ኃይለመለኮት መዋዕል ሰኔ ፩፮ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ ይፋት አውራጃ ማጀቴ ተወለዱ።
ሊቀ ትጉሃን ኃይለጊዮርጊስ ዳኜ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1881 - 1931]
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
በመርሐቤቴ ረመሸት ቀበሌ ደን አቦ በሚባል አካባቢ የተወለዱት ኀሩይ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያሳዩት በነበረው ትጋትና ቅልጥፍና ፀሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ቀድሞ ይጠሩበት የነበረውን ገብረመስቀልን በመቀየር ኀሩይ አሏቸው።
ለዓፄ ኃይለሥላሴ የቅርብ አማካሪ በመሆን የሃይማኖትና የአስተዳደር ሕጎች እየተረጎሙና የአርትኦት ሥራዎቻቸውን እያጠናቀቁ እንዲወጡ ያደረጉት ብላቴን ጌታ ኀሩይ ታሪክ፣ ማኀበራዊ ጉዳይንና ፍልስፍናን ያካተቱ 42 የሚደርሱ መጻሕፍትን አሳትመዋል፡፡ ከሥራዎቻቸው መካከል
“ወዳጄ ልቤ”
የሚባለው መጽሐፍ ታዋቂነትንና ተወዳጅነትን አትርፎላቸዋል።
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን መሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው ካሌንደር።
በመርሐቤቴ ረመሸት ቀበሌ ደን አቦ በሚባል አካባቢ የተወለዱት ኀሩይ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያሳዩት በነበረው ትጋትና ቅልጥፍና ፀሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ቀድሞ ይጠሩበት የነበረውን ገብረመስቀልን በመቀየር ኀሩይ አሏቸው።
መጻሕፍት ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ
ይጫኑ
ተመዝግበው ከሆነ እዚህ
ይጫኑ
[
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ቋንቋ
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
]
[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com