ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
አበጀ አያልነህ ሙላት
የደራሲው ሥራዎች
1.   አሌክሳንደር ፑሽኪን(ታሪክ)
2.   ጥገት ላም(ግጥምና ቅኔ)
3.   ማን ይኾን የበላ(ግጥምና ቅኔ)
4.   እሳት ሲነድ(ተውኔት)
5.   ድኻ አደግ(ተውኔት)
6.   ጋለሞታዋ(ተውኔት)
7.   ድርብ ጭቁን(ተውኔት)
8.   የገጠሯ ፋና(ተውኔት)
9.   የመንታ እናት(ተውኔት)
10.   ሻጥር በየፈርጁ(ተውኔት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
አያልነህ ሙላቱ በቀድሞው አጠራር በጎጃም ጠቅላይ ግዛት ኀዳር ፩፪ ቀን ፲፱፵፩ ዓ.ም. ተወለዱ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአገው ምድር፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በደብረ ማርቆስ ትምህርት ቤቶች ተከታትለዋል። የከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ አ.አ. ዩኒቨርሲቲና የወቅቱ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኀበር ባስገኘላቸው ነፃ የትምህርት ዕድል በመጠቀም በቀድሞዋ ቦቪየት ኀብረት፣ “በሞስኮ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ” በሥነ ጽሑፍና በጋዜጠኝነት በኤም.ኤ. ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡

አያልነህ ሙላቱ “እሳት ሲነድ”፣ “የገጠሯ ፋና”፣ “የመንታ እናት”፣ “ዱባና ቅል”፣ “ጥበበኛዋ ጋለሞታ”፣ “ሰባራ ዘንግ”፣ “ዶ/ር ጋጋኖ” ወዘተ የተሰኙ ተውኔቶችን ለሕዝብ አቅርበዋል፡፡ አያልነህ ሙላቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም “ዓለም”፣ “ቅሪት”፣ “ቀዝቃዛው ትዳር” “ጧሪ ልጆች”፣ “ባል እና ሚስት”፣ “ግርዛት”፣ “መስከረም”፣ “ቡሄ”፣ “የእናት ጡት”፣ “ያለ ዕድሜ ጋብቻ”፣ የተሰኙ ድራማዎች ታይተውላቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሬዲዮም “ቤተሰብ”፣ “ሴት ተማሪ”፣ “ጠለፋ”፣ “ዶ/ር ሙሉ፣ “ሴት ለጓዳ”፣ “ሕግና ሕጋዊነት” ወዘተ . . . . የተሰኙ ተውኔቶችን ለሕዝብ አቅርበዋል፡፡

አያልነህ ሙላቱ፤ “የሥነ ጽሑፍ ቅኝት”፣ “የአሌክሳንደር ፑሽኪን አጭር የሕይወት ታሪክ”፣ “ማን ይሆን የበላ?”፣ “ጥገት ላም”፣ የተሰኙ መጻሕፍትንም ለኀትመት አብቅተዋል፡፡ “ጽጌረዳ ብዕር”፣ እና “ትግላችን”፣ በተሰኙ የሥነ ግጥም መድብሎች ውስጥም፣ ከሌሎች ደራስያን ጋር በመሆን ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡ በሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸውም ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ለማግኘት በቅተዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com