ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ
[1885 - 1972]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ዓለማዊ ትግል(ግጥምና ቅኔ)
2.   ፊታውራሪ በላይ(ተውኔት)
3.   ሰውና እውቀት(ተውኔት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት በጉርሱም አውራጃ ኀዳር 1885 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በወራት ጊዜ ውስጥ እናታቸው ሞቱ፡፡ ዕድሜያቸው አራት ዓመት ሲሆናቸው ወላጆቻቸው ከሞቱባቸው ሌሎች ልጆች ከሚያድጉበት ከራስ መኮንን ቤት እየተማሩ እንዲያድጉ ተላኩ፡፡ እዚያም በአብዛኛው ግዕዝና ሌሎች ትምህርቶች ተማሩ።

እምሩ ኃይለሥላሴ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጣም ይታወቃሉ፡፡ ከምኒልክ ጊዜ ጀምሮ እስከ ደርግ ሥርዓት ድረስ መኖራቸው ደግሞ በበለጠ ለመታወቅ አስችሏቸዋል፡፡ ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ ከሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ዲፕሎማሲና ወታደራዊ ታሪክ አጉልተው ጽፈዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com