ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ደ/ር ዮናስ አድማሱ
[1935 - 2005]
የደራሲው ሥራዎች
1.    ዮፍታሔ ንጉሤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ(ታሪክ)
2.   እነ እስከማእዜኑ...(ግጥምና ቅኔ)
3.   ጊዜን ተፍቼበት(ግጥምና ቅኔ)
4.   ምኞት ፈረስ ቢኾን(ግጥምና ቅኔ)
5.   ዕፀ በለስ(ግጥምና ቅኔ)
6.   ጉራማይሌ(ግጥምና ቅኔ)

ስለደራሲው በጥቂቱ

ዶ/ር ዮናስ አድማሱ በ1935 ዓ.ም አዲስ አበባ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ የቄስ ትምህርት ተከታትለዋል። የዘመናዊውን የመደበኛ ትምህርት የተቀላቀሉት እድሜያቸው ዘጠኝ አመት ሲሞላ ነበር፤ የመደበኛ ትምህርታቸውን በኮከበ ጽብሐ ትምህርት ቤት ተከታትለው እንደጨረሱ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በመቀጠል በ1959 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀበሉ። ለተጨማሪ ትምህርት ወደ አሜሪካን ሀገር ከመጓዛቸው በፊት እንደተመረቁ ወዲያውኑ በተማሩበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአስተማሪነት ተቀጥረው የማገልገል እድል አግኝተዋል። በአሜሪካን ሀገር ካሊፎርኒያ ዪኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ተከታትለው በሶሺዮ-ሊንጉስቲክስ Socio-Linguistics የኤምኤ/MA ዲግሪያቸውን ከካሊፎርኒያ የኒቨርሲቲ ሎስአንጀለስ ተቀብለዋል። በ1962 ዓ.ም. ትምህርታቸውን በመቀጠል በአፍሪካ ጥናት/African Studies Programme እንዲሁም የዶክትሬት/PhD ዲግሪያቸውን በComparative Literature ቀድመው ከተማሩበት ከካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ሎስአንጀለስ ዩኒቨርሲቲ ተቀብለዋል።

ዶ/ር ዮናስ አድማሱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለበርካታ አመታት በተለያየ የሃላፊነት ቦታ በመያዝ በአስተማሪነት፣በተመራማሪነት፣በአስተዳደር እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባል በመሆን ከዚች አለም በአጸደ ሕይወት እስከተለዩባት የካቲት 1,2005 ዓ.ም. ድረስ በቀናነትና በትጋት ሀገራቸውን አገልግለዋል።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com