ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ተስፋዬ ገሰሰ
የደራሲው ሥራዎች
1.   መተከዣ(ግጥምና ቅኔ)
2.   ጥላሁን ግዛው(ተውኔት)
3.   ዕቃው(ተውኔት)
4.   የሺ(ተውኔት)
5.   አባትና ልጆች(ተውኔት)
6.   ላቀችና ደስታ(ተውኔት)
7.   ተሐድሶ(ተውኔት)
8.   መተከዣ(ልብወለድ)
9.   ዑመር ኻያም ልቦለዳዊ የሕይወት ታሪኩና ሩብአያቶቹ( ትርጉም)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ተስፋዬ ሐረርጌ ውስጥ ልዩ ስሙ ጎሮ ጉቱ በሚባል አካባቢ በ፲፱፳፱ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በልጅነታቸው ወላጆቻቸው በሞት ስለተለዩዋቸው አዲስ አበባ ዘመድ ቤት በመቀመጥ ትምህርታቸውን ተከታተሉ፡፡ የተፈሪ መኮንን ተማሪ በነበሩበት ወቅት ብዙ መጻሕፍት ከማንበብ ይልቅ እግር ኳስና ሌሎች ጨዋታዎችን ያዘወትሩ ነበር። በተለይ ግን የከበደ ሚካኤልን "የትንቢት ቀጠሮ" ተውኔት ይወዱ እንደነበር ይናገራሉ፡፡
በ፲፱፵፰ ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ገቡ፡፡ የፊልም ወይም የመድረክ ተዋናይ የመሆን ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም አጠቃላይ ጥበብ ጄኔራል አርትስ ሜጀር አድርገው የሕግ ትምህርት አጠኑ፡፡
የዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመረቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ሄደው ለሁለት ዓመታት ቆይተዋል፡፡
"የቴያትር ጥበብን በማጥናት በኢትዮጵያ ያለውን የቴያትር ባህል ለማሳደግ" በቆራጥነት የተነሱት አሜሪካ እያሉ ነበር፡፡ ቴያትር እንዲያጠኑ ሐሳቡን የጫሩባቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴያትር ባሳዩበት ወቅት በአተዋወን ብቃታቸው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተደስተው ሰዓት በመሸለም "ቴያትር" እንዲያጠኑ ከነገሯቸው በኋላ ነው፡፡
ከአሜሪካ በ፲፱፶፬ ዓ.ም. ከተመለሱ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴያትር ቤት በመቀጠር የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ሥራ የሆነውን "የሾህ አክሊል"ን በማዘጋጀትና የዋና ገፀባህሪውን በመወከል ተውነዋል፡፡ "የሺ" የሚል ተውኔት በመጻፍም ለመድረክ አብቅተዋል፡፡ በ፲፱፶፫ ዓ.ም. በእንግሊዝኛ ቋንቋ "ላቀችና ማሰሮዋ" የሚል ተውኔት ደርሰዋል፡፡
በርካታ ተውኔቶች ላይ የትወና ችሎታቸውን ያስመሰከሩ አጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞቻቸው በሩሲያኛ ተተርጉመው ሩሲያ ውስጥ ታትመዋል፡፡ የኡመር ካየምን መጽሐፍ "ሩብ አያት" በማለት ተርጉመው አሳትመዋል፡፡ በተጨማሪም በ፲፱፷፭ ዓ.ም. መተከዣ የሚል መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com