ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ Asefa Gebremariam Tesema
[1912 - 1961]
የደራሲው ሥራዎች
1.   የመስከረም ጮራ(ግጥምና ቅኔ)
2.   The Voice(ግጥምና ቅኔ)
3.   ዋናው ተቆጣጣሪ(ተውኔት)
4.    ዩሊየስ ቄሳር - ተውኔት -( ትርጉም)
5.   ከለንደን አዲስ አበባ(ተውኔት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
አቶ አሰፋ ገ/ማርያም ተሰማ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርበኞች ት/ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጄኔራል ውንጌት ት/ቤት ተምረዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በቀድሞው ሶቪየት ኀብረት ሌኒን ግራድ ዩኒቨርሲቲና በእንግሊዝ ሀገር በሚገኘው ኢንደንብራ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ሰልጥነዋል፡፡

ለኀትመት የበቁላቸው ሥራዎች "የመስከረም ጮራ"፤ እና “The Voice” የተሰኙ የግጥም መድብሎች ይጠቀሳሉ፡፡ በቲአትር ዘርፍ "ዩሊየስ ቄሳር"፣ "ዋናው ተቆጣጣሪ" የትርጉም ሥራዎች እና "ከለንደን አዲስ አበባ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ወጥ ቲአትር ለመድረክ አብቅተዋል፡፡ የደርግ ዘመንን ብሔራዊ የሕዝብ መዝሙርም ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኀበርን በዋና ፀሐፊነት መርተዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com