ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ደበበ ሰይፉ
[1942 - 1992]
የደራሲው ሥራዎች
1.   የብርሃን ፍቅር(ግጥምና ቅኔ)
2.   ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ(ግጥምና ቅኔ)
3.   ከባሕር የወጣ ዓሣ(ተውኔት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
በሲዳሞ ክፍለ ሀገር ይርጋዓለም ከተማ ሐምሌ 5 ቀን በ፲፱፵፪ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የርጋለም ከተማ በሚገኘው በራስ ደስታ ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃን በኮከበ ፅባሕ አዲስ አበባ ውስጥ ተከታትለዋል። የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ የመጀመሪያ፣ በእንግሊዝኛ ሥነ ጽሑፍ ደግሞ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

በአጫጭር ድርሰት በግጥምና በቴያትር እንዲሁም በሂስ ሥራቸው በብዙዎች ዘንድ የሚታወቁት ደበበ ሰይፉ የሀገሪቱ የሥነ ጽሑፍ እድገት ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርስ ጥረት ያደረጉ ምሁር ነበሩ፡፡ በ፲፱፷፮ ዓ.ም. "ሣይቋጠር ሲተረተር" የሚል ድራማ ጽፈው በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ታይቷል፡፡

"የብርሃን ፍቅር" በሚል ርዕስ ያሳተሙት ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 የግጥም ስብስብ መጻሕፍታቸው ብዙዎች ዘንድ አድናቆት አትርፈዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com