ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ግርማቸው ተክለሐዋርያት
[1906 - 1979]
የደራሲው ሥራዎች
1.   አርኣያ(ልብወለድ)
2.   ቴዎድሮስ(ተውኔት)
3.   ዐደዋ(ተውኔት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ደጃዝማች ግርማቸው ተክለሐዋርያት በሐረር ጠቅላይ ግዛት ሒርና ወረዳ በ1906 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአማርኛ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ወደ ድሬደዋ ተዛውረው የፈረንሳይኛ ቋንቋ አጥንተዋል። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥተው በአሊያንስ ፍራንሴ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ወደ ፈረንሳይ ሀገር ሄደው የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ጨርሰው ተመረቁ፡፡ ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ በኋላም የደጃዝማች ማዕረግ የተሠጣቸው ሲሆን በተለያዩ የመንግሥት መ/ቤቶች በኃላፊነት ሠርተዋል፡፡ አምባሳደር በመሆንም በተለያዩ አገራት አገልግለዋል፡፡

ደጃዝማች ግርማቸው ተክለሐዋርያት በሥነ ጽሑፍ ረገድ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው መካከል “አርአያ” በሚል ርዕስ የጻፉት ልቦለድ መጽሐፍ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ከማትረፉም ባሻገር በትምህርት ሚኒስቴር አማካይነት ለመማሪያነት ተመርጦ በወቅቱ ለወጣቶች የኀሊና ብርሃን ለመሆን ችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ደራስያን እንዲበረታቱ የድርሰት ሙያቸውም እንዲዳብርና እንዲስፋፋ የደራስያን ማኀበር በማቋቋምና የግል ገንዘባቸውን በመለገስ ለሙያው የነበራቸውን ታላቅ አክብሮትና ፍቅር በተግባር አሳይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ድርሰት ማኀበርንም በፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com