ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
በእምነት ገብረአምላክ
የደራሲው ሥራዎች
1.   ልጅነት ተመልሶ አይመጣም(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
በእምነት የተወለዱት በ፲፱፲፫ ዓ.ም. ነበር፡፡ በኤርትራ ገጠራማ አካባቢ የተወለዱት በእምነት ከቤተሰቦቻቸው ጋር አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በስዊድን የሚሲዮን ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን መከታተል ቢጀምሩም በጣሊያን ወረራ ምክንያት ለማቋረጥ ተገደዋል፡፡ ቀጥሎም ጣሊያን ኮንስላታ ትምህርት ቤት በመግባት ትምህርታቸውን ቀጥለው በቤተሰብ ችግር ምክንያት አቋርጠዋል፡፡ ለጣሊያኖች በፎቶግራፍ አንሺነት ተቀጥረው ሰርተዋል፡፡ የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ በኃይል ተሸንፎ ከተባረረ በኋላ በፖሊስ ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት ለስድስት ዓመታት አገልግዋል፡፡ ወደ አሜሪካ በመሄድ ትምህርት መማር ቢጀምሩም በአየር አለመስማማት ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል በ፲፱፶፰ ዓ.ም. በቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ በማዕረግ ተመረቁ፡፡ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የማስተማር ዕድል አጋጥሟቸው በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ለመሥራት አሜሪካ የሄዱ ቢሆንም ነገር ግን የቤተሰብ ችግር ስላጋጠማቸው ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ለመመለስ ተገደዋል፡፡

ለአማርኛ ቋንቋ ማደግ ይከራከሩ የነበሩት በእምነት የተለያዩ የትርጉም ሥራዎች ቢኖሯቸውም በእጅጉ የሚታወቁት ግን “ልጅነት ተመልሶ አይመጣም” በሚለው ተወዳጅ ድርሰታቸው ነው፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ ካሌንደር።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com