ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው
[1883 - 1953]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ያይኔ አበባ(ልብወለድ)
2.   አልሞትኹም ብዬ አልዋሽም(ተውኔት)
3.   ተዎድሮስ ጣይቱ ብጡል(ልብወለድ)
4.   ዦሮ ጠቢ(ልብወለድ)
5.   የድኾች ከተማ(ልብወለድ)
6.   ፀሓይ መስፍን(ልብወለድ)
7.   መልካም ቤተሰቦች(ታሪክ)
8.   ሣልሳዊ ዳዊት(ተውኔት)
9.   አርሙኝ(ፍልስፍና)
10.   የቃየል ድንጋይ(ተውኔት)
11.   ዓለም ወረተኛ(ተውኔት)
12.   የደም ድምፅ(ተውኔት)
13.   አሳብና ሰው(ተውኔት)
14.   የማይጨው ጦርነት ባጭሩ የዓለም ታሪክ(ታሪክ)
15.   ከቡቃያ እስከ መከር(ልብወለድ)
16.   የሕልም ሩጫ (ታሪክ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው በሰሜን ሸዋ በተጉለት አውራጃ አዲስጌ በምትባል ቦታ በ በ1983 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በዳግማዊ ምኒልክ፣ በንግሥት ዘውዲቱ እና በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሀገራቸውን አገልግለዋል።

በሕይወት ዘመናቸው ከ2ዐ በላይ መጻሕፍት በመድረስ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ዕድገት የጎላ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ከሥነ ጽሑፍ ሥራዎቻቸው ውስጥ የታተመው “አርሙኝ” የተባለው መጽሐፋቸው በብዙዎች ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ የሕይወት ታሪካቸውን ባጭሩ፣ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት የጻፏሕውን ድርሰቶችን ስለማይጮው ጦርነትና የዓለም ፖለቲካ በማካተት የጻፉት ነው፡፡ “የድሆች ከተማ” በ1933፣ “ሐሳብና ሰው” በ1933፣ “ሣልሳዊ ዳዊት” በ1933 “የፍቅር ጮራ” በ1939፣ ከጻፏቸው መጽሐፍት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com