ታደለ ገ/ሕይወት ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፲፱፴፰ ዓ.ም. በግዮን አምቦ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞው ቀ.ኃ.ሥ. ኮከበ ጽባሕ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ተምረው በፖለቲካል ሳይንስና ሥነ-መንግሥት ትምህርት በዲፕሎማ ተመርቀዋል።
ታደለ ገ/ሕይወት “ማነው ኢትዮጵያዊ?”፣ “ኢትዮጵያ ትቅደም”፣ “ከርሞ ዘማች” “ተራማጅ ጥቅሶች”፣ “ለቀዩ አበባ”፣ “ብቀላ” የተሰኙ የፈጠራና የትርጉም ሥራዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |