ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ገ/መስቀል ገበየሁ አየለ
የደራሲው ሥራዎች
1.   ጣምራ ጦር(ልብወለድ)
2.   ስደተኛው(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ገበየሁ አየለ ጥቅምት ፳፰ ቀን ፲፱፴፮ ዓ.ም. በቀድሞ ሸዋ ክ/ሀገር ጌቶ ቀበሌ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሚያዝያ 27 ት/ቤት ጅማ ከተማና አዲስ አበባ ተስፋ ኮከብ እና አስፋወሰን ት/ቤቶች ጨርሰዋል። ከዚያም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ “ብሪቲሽ ቱቶሪያል ኮሌጅ” በመላላክ የትምህርት ፕሮግራም ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡ የከፍተኛ ወታደራዊ ትምህርታቸውን ደግሞ በኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ ተከታትለዋል፡፡

ገበየሁ አየለ በአፍሮ ኤሺያ ደራስያን ጉባኤ ኮንጎ ብራዛቪል በመገኘት የኢትዮጵያ ደራስያንን ወክለው ተሳትፈዋል፡፡

ገበየሁ አየለ “ጣምራ ጦር”፣ “ስደተኛው”፣ “ዕንባና ሳቅ” እና “ረመጥ” የተሰኙ ረጃጅም ልቦለዶችና አያሌ አጫጭር ልቦለዶችን እንዲሁም ከአሥር በላይ የሚሆኑ የሕጻናት መጻሕፍትን አበርክተዋል፡፡ በተጨማሪም “ሥውር ሰይፍ” የተሰኘ ድራማ ለሕዝብ ዕይታ አብቅተዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com