ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
አንድአርጌመስፍን ሽፈራው Andargemesfine Shiferaw
የደራሲው ሥራዎች
1.   ደም በደም(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
አንዳርጌ መስፍን ሚየዝየ ፰ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. ልዩ ስሙ “አባጭመና መስክ” በተሰኘ ቀበሌ ጎንደር ክ/ሃገር ተወለዱ። ከ፲፱፶፪ - ፲፱፶፬ ዓ.ም. በቤተክህነት ውስጥ የቀለም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ከ፲፱፶፭ - ፲፱፷፪ ዓ.ም. የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በተወለዱበት ቀበሌ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እስከ ፲፱፷፮ ዓ.ም. ጎንደር ከተማ ውስጥ ተምረዋል፡፡ ከ፲፱፹፪ - ፲፱፹፬ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት የተከታተሉ ሲሆን በጦር ሠራዊት ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ ስለአየር መቃወሚያና ሌሎች ወታደራዊ ዘዴዎች ተጨማሪ ዕውቀት አግኝተዋል፡፡

አንዳርጌ መስፍን “ዳር እስከዳር”፣ “ጥቁር ደም”፣ “ጥልፍልፍ”፣ “ቅሌት”፣ “ደም በደም” በሚሉ ርዕሶች የተጻፉ ልቦለድ ሥራዎች አሉዋቸው፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com