ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ሲራክ ኅሩይ ወልደሥላሴ
[1903 - 1975]
የደራሲው ሥራዎች
1.   የራስሤላስ መስፍነ ኢትዮጵያ ታሪክ( ትርጉም)

ስለደራሲው በጥቂቱ
የአባታቸውን የሥነ ጽሑፍ ሥራ በሥራ ላይ ያዋሉ፣ የአባታቸውን የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች በጥንቃቄ ይዘው የቆዩ፣ ከፊሎችን እንደገና ያሳተሙ ነበሩ፡፡ ከአለቃ ገብረሐና በኋላ እንደ ሲራክ ያሉ የሚያስቁ ቀልዶችን በሰፊው ያሠራጨና ያስተላለፈ ማንም ፀሐፊ የለም።

ሲራክ መጀመሪያ ግዕዝ ለመማር ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም ተላኩ፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ ከማሲዮኖች ት/ቤት ገቡ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለመማር ወደ ግብጽ አሌክሳንድርያ ኮሌጅ ሄዱ፡፡ ከኢጣሊያ ወረራ በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ እንግሊዝ ሀገር ተጓዙ፡፡ ሲራክ ፍልስፍና ለመማር ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ገቡ።

ዓፄ ኃይለሥላሴ በ1903 ዓ.ም. ከስደት ከተመለሱ በኋላ ሲራክ የሀገር ግዛት ሚኒስትር ፀሐፊ በመሆን ተሾሙ፡፡ ከዚያም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዛወሩ፡፡ በኋላም ወደ ሕንድ በአማካሪነት ተልከው አገለገሉ፡፡ በመንግሥት ሥራ ላይ እያገለገሉ ሳሉ ብዙ ሚኒስትሮች ስለሚቀበሉት ጉቦ፣ ሁኔታዎችን ማዘግየትና ማስተላለፍ ፖሊሲያቸውን አጥብቀው ይቃወሙ ነበር፡፡ ሲራክ እምቅ ዕውቀት እንዳላቸው ቢታወቅም ከንጉሱ ፖለቲከኞች ጋር ለመጫወት ያልፈለጉ ሀቀኛ ሰው ነበሩ፡፡ ንጉሡም ቢሆን ፖሊሲያቸውን እስካልለወጡ በሀገሪቱ አብዮት እንደሚነሳባቸው ነግረዋቸው ነበር፡፡ ያለአግባብ በሚፈጸሙ ጥፋቶች ላለመጠየቅ ከመንግሥት ሥራ ለቀው ወጡ፡፡

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከኢትዮጵያ ድንበር ውጭ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች እንግሊዝ ቆንስላ ውስጥ ከሚሠራና የእንግሊዝ የመረጃ አገልግሎት ሠራተኛ ከሆነ ሰው ጋር ተዋወቁ፡፡ በኋላም ወርሃዊ መጽሔት ያዘጋጅ ስለነበር ሲራክም አንዳንድ ጽሑፎችን በአማርኛ እየተረጎሙ ለማዘጋጀት ተቀጠሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ነበር በእንግሊዝ ቆንስላ ውስጥ በመረጃ አገልግሎት ቢሮ የሚሠራው ዎርዝ የተባለው ሰው ሲራክን የዶክተር ሳሙኤል ጆንሰንን “ራሴላስ” እንዲተረጉሙ አደረገ፡፡ ሲራክ ይህን መጽሐፍ “የአቢሲኒያው ልዑል” በማለት ተርጉመው አሳተሙ፡፡ እኝህ ሰው በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com