ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ቀኛዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ ዘብሔረ ቡልጋ
[1895 - 1992]
የደራሲው ሥራዎች
1.   መዝገበ ሐዋርያ(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ቀኛዝማች ተስፋ በሰሜን ሸዋ በቡልጋና በረኸት ክታብ ወይራ አክርሚት ከተባለ ቀበሌ በ1895 ዓ.ም. ታህሣሥ 24 ቀን ተወለዱ።

በአባታቸው አማካኝነት በአራት ዓመት ከአራት ወር ከአራት ቀን ሲሞላቸው ፊደል ቆጠሩ፡፡ ቀጥሎም ንባብ፣ ዳዊትና ውዳሴ ማርያም መልክዓ ማርያምና መልክዓ ኢየሱስን አጠናቀው በመማር የዲቁና ማዕረግ ተቀብለዋል፡፡ ቀኛዝማች ተስፋ ቤተክርስቲያንን በዲቁና እያገለገሉ የወላጅ አባታቸውን አርአያ በመከተ የፍየል ቆዳ እየፋቁ በመድመፅ እየደመፁ፣ ብራና በማዘጋጀት፣ ቀለሙን ከልዩ ልዩ ዕፅዋት እያነጠሩ፣ በብዕር እየጻፉ የዘወትር ጸሎት ሰዓታት ዘሌሊት፣ መዝገበ ሐዋርያ ሌላም መጻሕፍትን እየጻፉ በማራባት አሰራጭተው ሕብረተሰቡ እንዲጠቀም አድርገዋል፡፡

በ1921 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ቄርሎስ በቤተ ክህነት ግቢ ቦታ ስለሰጧቸው በሰው ኃይል የሚሠራ የማተሚያ ማሽን ገዝተው ከፊደል ገበታ ጀምሮ ያሉትን የንባብ መማሪያ፣ የጸሎትና የሃይማኖት መጻሕፍትና በራሳቸው የተደረሱ መጻሕፍት ግጥምን ሌሎች ጽሑፎችን ያትሙ ነበር፡፡ በተጨማሪ የዩፍታሔ ንጉሤና የሌሎች ታዋቂ ደራስያንን ሥራ አትመዋል፡፡ በዚህም ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ዕድገት አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ በተለይ ግን ያዘጋጃቸው በነበሩት ልዩ ልዩ የፊደል ገበታዎች ያልተማረ ኢትዮጵያዊ የለም ማለት ይቻላል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com