ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ሣህለስላሴ ብርሃነማርያም
የደራሲው ሥራዎች
1.   ሹክታ(ወግ)
2.   አፈርሳታAfersata(ልብወለድ)
3.   የሁለት ከተሞች ወግ( ትርጉም)
4.   The warrior king(ልብወለድ)
5.   የሸንጋይ መንደር(ልብወለድ)
6.   ወጣት ይፍረደው፤ አፈርሳታ(ልብወለድ)
7.   መከረኞች( ትርጉም)
8.   እምዩ( ትርጉም)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም በቀድሞው አጠራር ሸዋ ክፍለሀገር በሚባለው በጨቦና ጉራጌ ተወለዱ፡፡ የ1ዐኛ ክፍል ተማበ በነበሩበት ወቅት አባታቸው በመሞታቸው የቤተሰብ ኃላፊ ለመሆን ተገደዋል።

በብዛት የፍልስፍና እና የሥነ ጽሑፍ መጻሕፍትን ያነባሉ፡፡ ለሚጽፏቸው መጻሕፍት የፍልስፍና መሠረት እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡ ለዚህ ዓለም ያላቸውን አዎንታዊ አመለካከት ለአንባቢየቸው ለማሳየት ይፈልጋሉ፡፡

ሳህለሥላሴ ከሎስአንጀለስ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ብዙም አልሠሩትም፡፡

በፕሮፌሰር ዎልፍ ሌስላው አማካኝነት የመጀመሪያውን መጽሐፍ "የሸንጋይ መንደር" በሚል ርዕስ ጽፈዋል፡፡ መጽሐፉ በእንግሊዝኛ ተተርጉሟል፡፡"ወጣት ይፍረደው፤ አፈርሳታ" እና ሌሎች ድርሰቶችን ጽፈዋል፡፡ የሁለት ከተሞች ወግ፣ መከረኞችና እምዩ ከትርጉም ሥራዎቻቸው መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com