ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
አማረ ማሞ
የደራሲው ሥራዎች
1.   የልብ ወለድ ድርሰት አጻጻፍ(ትምህርት)
2.   አሳረኛው( ትርጉም)
3.   የቀለም ጠብታ(ትምህርት)
4.   የእውነት ብልጭታ(ተውኔት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
አማረ ማሞ በ፲፱፴፱ ዓ.ም. በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ፊደል በመቁጠር ዳዊት ደግመዋል፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለው በሥራ ዓለም በቀድሞው የምሥራች ድምፅ ውስጥ የሥነ ጽሑፍ ኃላፊ ሆነው ከማገልገላቸውም በተጨማሪ የትርጉም ሥራዎች ሠርተዋል።

አማረ ማሞ ለረጅም ዓመታት የኢትዮጵያ መጽሐፍት ድርጅት ም/ሥራ አስኪጅ በመሆን አገልግለዋል፡፡ የተለያዩ ድርሰቶችን በመድረስና የትርጉም ሥራዎችን በማዘጋጀት ከሰላሳ በላይ መጻሕፍት አሳትመዋል፡፡ ከ፲፱፷፮ ዓ.ም. በኋላም በርካታ ወይ ድርሰቶችንና የድርሰት መማሪያ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅተዋል። ከነዚህም መካከል በ፲፱፷፰ ዓ.ም. "የልብ ወለድ ድርሰት አጻጻፍ"፣ በ፲፱፸፮ ዓ.ም. "የቀለም ጠብታ" እና በ፲፱፹፬ ዓ.ም. "አሳረኛው"፣ በሚል የታተመው የትርጉም ሥራም ተጠቃሾች ናቸው። ለሀገራችን የሥነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ደራስያን ማኀበር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በመሆን አገልግለዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን መህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com