ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
አስፋው ተፈራ Asfaw Tefera
የደራሲው ሥራዎች
1.   መክሰተ ሰዋሰው (ትምህርት)
2.   የቤተክርስቲያን ታሪክ ለሕጻናት መማሪያ(ትምህርት)
3.   ጠቅላላ የጂኦግራፊ መጽሐፍ (ትምህርት)
4.   የአፍሪካ ጂኦግራፊ አጭር የዓለም ታሪክ(ትምህርት)
5.   Africa past present and future(ትምህርት)
6.   West African Politics(ምርምር)
7.   Africa March to Unity(ምርምር)

ስለደራሲው በጥቂቱ
በ፲፱፳፫ ዓ.ም. በአሰበ ተፈሪ ደጋማው ክፍል ልዩ ስሙ ካራቆሬ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ፡፡ አቶ አስፋው ተፈራ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሰበ ተፈሪ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ተግባረዕድ ት/ቤት ቴክኒክና ሙያ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ መምህራን ማሠልጠኛ በመግባት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፣ በለንደን ስኩል ኦፍ ኦሪየንታል ኤንድ አፍሪካ ጉዳዮች ጥናት በዲግሪ፣ በሕዝብ አስተዳደር ደግሞ በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡

ከአሥራ ሁለት በላይ የታተሙ ሥራዎች አሏቸው፡፡ ከኀትመት ውጤታቸው መካከል የቤተክርስቲያን ታሪክ ለሕጻናት መማሪያ፣ ጠቅላላ የጂኦግራፊ መጽሐፍ፣ የአፍሪካ ጂኦግራፊ አጭር የዓለም ታሪክ፣ መክሰተ ሰዋሰው ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የቼምበር ማተሚያ ቤት፣ የኢምፔሪያል ሆቴልና የኢምፔሪያል አግሮ ኢንዱስትሪ ባለቤት ናቸው፡፡

በአማርኛ ካሳተሟቸው መጻሕፍት ሌላ በእንግሊዝኛ ቋንቋ “አፍሪካ ፓስት ፕሬዘንት ኤንድ ፊውቸር”፣ “ዌስት አፍሪካን ፖለቲክስ”፣ “አፍሪካ ማርች ቱ ዩኒት” በሚሉ ርዕሶች መጻሕፍት ጽፈው አሳትመዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com