ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ታደሰ ሊበን
የደራሲው ሥራዎች
1.   ሌላው መንገድ(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
በጻፏቸው አጫጭር ልብ ወለዶች የሚታወቁት ታደሰ ሊበን በ፲፱፳፫ ዓ.ም. ወለጋ ውስጥ ደንቢዶሎ ተወለዱ። ገና የስድስት ዓመት ልጅ እያሉ አባታቸው ሞተውባቸዋል። እናታቸው ጥሩ ጥሩ ተረቶች እየተረኩላቸው ያደጉት ታደሰ ሊበን የልብወለድ ፍቅር ያደረባቸው በዚያን ጊዜ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡

ከመንግሥቱ ለማ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ ነገር ግን በ፲፱፵፱ ዓ.ም. “መስከረም” እና በ፲፱፶፪ ዓ.ም. “ሌላው መንገድ” በሚል ርዕስ የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ ካሳተሙ በኋላ ሌላ መጽሐፍ ባለማሳተማቸው ከመንግሥቱ ለማ ጋር ተቀያይመዋል፡፡

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአጭር ልብወለድ የመጀመሪያው ጸሐፊ በመባል ይታወቁ ነበር፡፡ ነገር ግን “የጉለሌው ሰካራም” ጸሐፊ ተመስገን ገብሬ የመጀመሪያው የአጭር ልብወለድ ጸሐፊ መሆናቸው ከታወቀ በኋላ ቀድሞ የነበረው አስተሳሰብ ቢቀየርም በሥነ ጽሑፍ እድገት ላይ ያደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ግን የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com