ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
መሪ ጌታ ግርማጽዮን መብራህቱ
የደራሲው ሥራዎች
1.   የሃይማኖት ጋሻ ለጠላት መመለሻ(ትምህርት)
2.   የትግርኛ መዝገበ ቃላት(ቋንቋ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
መሪጌታ ግርማጽዮን መብራህቱ በ፲፱፲፰ ዓ.ም. ኤርትራ ውስጥ ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢያቸው የቤተክርስቲያን ትምህርት እየተማሩ አደጉ፡፡ በየገዳማቱ እየተዘዋወሩ ጸዋት ወዜማ ተማሩ። ወደ ጎንደር ተጉዘውም የዜማና የአቋቋም ትምህርት አጠናቅቀው በመመረቅ ወደ ትውልድ ቀበሌያቸው በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመሪ ጌታነት እያገለገሉ ብራና ፍቀው ቆርጠውና ቀለም በጥብጠው ብዙ የብራና መጽሐፍትን ጽፈዋል፡፡

መሪጌታ ግርማጽዮን በቤተክርስቲያን ትምህርት ሙሉ ዕውቀት ያላቸው ከመሆኑም በላይ በዘመናዊ ትምህርት እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ድረስ ተምረዋል፡፡ በወሎ ክፍለ ሀገር ይሰጥ በነበረው የመምህራን ሥልጠና ተካፍለው በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ ለመማሪያነት የሚያገለግሉ የተለያዩ የአማርኛ መጽሐፍትም አዘጋጅተዋል፡፡ ቀደም ሲልም “የሃይማኖት ጋሻ ለጠላት መመለሻ” በሚል ርዕስ ስለኢትዮጵያ አንድነትና ስለ ሕዝቧ ጀግንነት የሚያወሳ መጽሐፍ ደርሰው አሳትመዋል፡፡ መሪጌታ ግርማጽዮን ታላቁንና የመጀመሪያውን የትግርኛ መዝገበ ቃላት ሲያዘጋጁ ያልዳሰሱት አውራጃ፣ ያላገላበጡት መረጃ አይገኝም፡፡ በስድስት መቶ ሃምሳ ገላጭ ሥዕሎች የተዘጋጀው “የትግርኛ መዝገበ ቃላት” ለትግርኛ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማበርከቱም በላይ ለማስተማሪያነትም ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡

ይህም ዐብይ ሥራቸው በሀገራችን የሥነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ነው፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com