ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ተሰማ ሀብተሚካኤል
[1882 - 1952]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ከሣቴ ብርሃን(ቋንቋ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ተሰማ ሀብተሚካኤል በሰሜን ሸዋ በሰላሌ አውራጃ ጎሐጽዮን በ፲፰፻፹፪ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ ተሰማ የአባይን ወንዝ አቋርጠው ወደ ጎጃም በመሄድ ዜማ፣ ትርጉም፣ ቅኔን በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተከታትለዋል፡፡ በተለይ ዲማ ወደሚገኘው እውቅ ገዳም በመሄድ ዜማና ቅኔ ተምረዋል። የቤተክርስቲያን ከፍተኛ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ በኋላ በ፲፱፻፩ ዓ.ም. በመንግሥት ሥራ በመቀጠር ወደ ሐረርጌ ጠ/ግዛት ሄዱ፡፡ ተሰማ በጥሩ እጅ ጽሑፋቸውና በተለየ የፊደል አጣጣላቸው ይታወቁ ነበር፡፡ ብዙ የሃይማኖት መጻሕፍት እንዲገለብጡ ይታዘዙ የነበረውም ለዚህ ነው፡፡ በጡረታ እስከተገለሉበት ፲፱፻፭፬ ዓ.ም. ድረስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት እንዲያዘጋጁ በትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ሠርተዋል፡፡ “ከሣቴ ብርሃን” የተሰኘው ሥራቸው ጠንካራ፣ ዋነኛና ትልቁ ሥራቸው ነው፡፡ ከ9"7 እስከ ከ9#7 ዓ.ም. በዚህ መዝገበ ቃላት ዝግጅት ላይ እንደነበሩ ብዙ ችግሮችና መሰናክሎች ገጥመዋቸዋል፡፡ አማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ቢሆንም እግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አደሪኛ እና ግዕዝ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ይህን የቋንቋ ዕውቀታቸውንም ሥራ ላይ አውለዋል፡፡ ጥንካሬያቸውንም “ከሣቴ ብርሃን” በተባለው መዝገበ ቃላት ዝግጅት ላይ ተገልጧል፡፡ በተለይ ይህንን መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት ያነሣሣቸው በመምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ውስጥ ሲሠሩ በነበረበት ጊዜ ተማሪዎች ለቃላት ትክክለኛውን ትርጉም የመስጠት ችግር እንዳለባቸው በመረዳት፣ ብዙ የአማርኛ ቃላት በከተሞች አካባቢ በመረሳታቸውና እየጠፉ በመምጣታቸው ለተተኪው ትውልድ መዝግበው ለማስቀመጥ በማሰብ ነው፡፡ ከአሥር ዓመታት በኋላ ባለ 1,398 ገጾች መዝገበ ቃላት ሲያዘጋጁ፣ መዝገበ ቃላቱም 33,000 ድርሰቶች፣ አገባቦች እና 1,278 ሥዕሎች ሲኖሩት ከ12 ዓመታት በኋላ በገበያ ላይ ለመዋል በቅቷል፡፡ ስሙም ለደራሲው ክብር ሲባል “ከሣቴ ብርሃን ተሰማ” እንዲባል በትምህርትና ሥነ ጥበብ ሚኒስቴር ተመርጦ ተሰየመ፡፡ ይህም ለተሰማ ሀብተሚካኤል እንደ ሽልማት ተቆጠረ፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com