ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ማህተመሥላሴ ወልደመስቀል
[1912 - 1966]
የደራሲው ሥራዎች
1.   እንቅልፍ ለምኔ(ወግ)
2.   ዝክረ ነገር(ታሪክ)
3.   ቼ በለው(ታሪክ)
4.   ኅልቈ ዘመን ዘንጉሥ ሣህለሥላሴ(ታሪክ)
5.   ያማርኛ ቅኔ(ግጥምና ቅኔ)
6.   ያማርኛ ቅኔ ከነመፍቻው(ግጥምና ቅኔ)
7.   ስለ ኢትዮጵያ የመሬት ሥሬት አስተዳደርና ግብር፣ ጠቅላላ አስተያየት።(ትምህርት)
8.   እጹብ ድንቅ(ልብወለድ)
9.   ያባቶች ቅርስ(ትምህርት)
10.   ጥበበ ገራህት(ትምህርት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
የፈረንሳይ አገር የግብርና ተማሪ የነበሩት ብላቴን ማኀተመ ሥላሴ ለልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን ጸሐፊና የእርሻ ሚኒስቴር ምክትል ዋና ሚኒስትር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሕዝብ አገልግሎት ሚኒስቴርና የዘውድ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል። በታሪክ ፊት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውና አጠቃላዩን የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበዊና ፖለቲካዊ ገጽታ የሚዘክረውን “ዝክረ ነገር መጽሐፍ” በ1942 ዓ.ም. ለኀትመት አብቅተዋል፡፡

በተጨማሪም “የአባቶች ቅርስ” በ1943 ዓ.ም.፣ “አማርኛ ቅኔ ነጠላ” በ1948 ዓ.ም.፣ “እንቅልፍ ለምኔ” በ1950 ዓ.ም.፣ “ያገር ባህል” በ1960 ዓ.ም.፣ “ባለን እንወቅበት” በ1961 ዓ.ም. እና ሌሎች መጽሐፍት አሳትመዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com