ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
መስፍን ሀብተማርያም ሞገስ
የደራሲው ሥራዎች
1.   አዜብና ሌሎች ዐጫጭር ድርሰቶች(ልብወለድ)
2.   ዓውደ ዓመት(ወግ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
መስፍን ሀ/ማርያም የካቲት ፳፭ ቀን ፲፱፴፮ ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ሞጆ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞጆ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃን በአንቦ ማዕርገ ሕይወት ት/ቤት አጠናቅቀዋል። የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ በቢ.ኤ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ በተጨማሪም ከብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ካናዳ በፈጠራ ድርሰቶች አጻጻፍ ኤም.ኤ. ዲግሪ ኤም.ኤፍ.ኤ ተቀብለዋል፡፡

“የቡና ቤት ሥዕሎችና ሌሎች ወጎች”፣ “ዓውዳመት”፣ “አዜብና ሌሎችም አጫጭር ልቦለዶች”፣ “የሌሊት ድምጾች” የሚሉ ልቦለድ ሥራዎችንና የወግ ጽሑፎችን ለንባብ አብቅተዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com