ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ደምሴ ጽጌ
የደራሲው ሥራዎች
1.   ፍለጋ(ልብወለድ)
2.   ምትሐት(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ደምሴ ጽጌ በአዲስ አበባ ከተማ ታኀሳስ ፳፩ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. ተወለዱ። ከ፲፱፶፪ ዓ.ም. ጀምሮ በስብስቴ ነጋሤ አንደኛ ደረጃ ት/ቤትና በሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተምረው የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በ ፩፱፷፫ አጠናቀቁ፣ ከዚያም በመምህርነት ሙያ ሠልጥነው ዲፕሎማ ካገኙ በኋላ በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ በቋንቋዎች ጥናት ተቋም ከኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ክፍል በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡

ደምሴ ጽጌ የተለያዩ ወጥና ትርጉም ሥራዎችን አሳትመው ለአንባቢያን ያቀረቡ ሲሆን፣ ከሥራዎቻቸው መካከልም “ፍለጋ”፣ “ምትሐት”፣ ከትርጉም ሥራዎቻቸው ደግሞ የጀምስ ሀድሌይ ቼዝን “ትንግርት”፣ ከሌሎች ደራስያን ጋር በመሆን “ጠብታ ማር”፣ አጫጭር ልቦለድ ጽሑፎች፤ ከባሴ ሀብቴ ጋር አሳትመዋል፡፡ እንዲሁም “ጭጋግና ጠል” በሚል ርዕስ በታተመ መድብል ውስጥ ከሌሎች ደራስያን ጋር በጋራ ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com