ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ተክለሐዋርያት ተክለማርያም
[1876 - 1969]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ስለትልቅ ሳልና ነቀርሣ የምክር ቃል(ትምህርት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
በ1876 ዓ.ም በሰኔ ወር በሳያድብር ተወለዱ፡፡ ፊታውራሪ ተክለሃዋርያት በልጅነታቸው በወንድማቸው አማካኝነት ከሸዋ ወደ ሐረር ጠቅላይ ግዛት ተጉዘው እራስ መኮንን ቤት አደጉ፡፡ በልጅነታቸው አልቀርም በማለት 50 ጥይት ጎራሽ ጠመንዣ ታጥቀው ወደ አድዋ ዘመቱ። ከጦርነቱ መልስ እራስ መኮንን ቃል በማስገባት አጼ ሚኒሊክ እንዲፈቅዱላቸው በማድረግ ወደ ሩሲያ ሄደው ትምህርት ቤት ገቡ። በሩሲያ ተልኳቸው ዘመናዊ የጦር ትምህርት ለአራት አመታት ተከታትለዋል።

ከሩሲያ መልስ መጀመሪያ የልጅ እያሱ አማካሪ በሇላም የአፄ ኃይለሥላሴ አማካሪ በመሆን በተለያየ የስልጣን እርከን በመሾም አገራቸውን አገልግለዋል። ከአገልግሎታቸው ውስጥ የከተማ ህግ ማርቀቅ፣ ዘመናዊ እርሻን ማስተዋወቅ፣ ከተማ መመስረትን ይገኝበታል። በተለይ ፊታውራሪ አፄ ሚኒሊክ ማረፋቸው ከተገለፀ በሇላ በልጅ እያሱና በአፄ ኃይለሥላሴ መካከል በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ ከሸዋ መኳንንት ጋር በማበር ሐረር የእያሱ የግል አማካሪ በነበሩበት ጊዜ ያዩትን የሰሙትን የልጅ እያሱን ስህተቶች በመግለጥ እንዲሁም ሇላ ጦርነት ጭምር በመግጠምና ድል በማድረግ የሸዋን መኳንንት ተቀላቅለዋል።

ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት በአማርኛ ድርሰት ግሩም ችሎታ ነበራቸው፡፡ ከፃፏቸው መጽሐፍት መካከል ፋቡላ የአውሬዎች ተረት ተውኔት፣ ታሪክና ምሳሌ 1ኛ መጽሐፍ፣ ትንሽ የእርሻ መፈተኛ የሚሉት ሲታተሙላቸው አውሮፓ በነበሩበት ጊዜ የፃፉዋቸው መንቶች እና ምድራዊ ኑሮ የተሰኙ ድርሰቶችም አሏቸው፡፡ እራሳቸው የፃፉት ኦቶባዮግራፊያቸው ለአገራቸው ከአበረከቱት ታላላቅ አስተዋጾ በተጨማሪ በጊዜያቸው የነበረውን አስተዳደር ሁኔታ ችግሮቹን፤ የተደረጉ ጥረቶችን እንዲሁም በሀገሪቱ የተካሄዱ ታላላቅ ክስተቶችን፣ በልዩ ሁኔታ እንዲሁ በልጅነታቸው የዘመቱበትን የአድዋ ጦርነት ውሎ እና በሩሲያና አውሮዻ ቆይታቸው ያሳለፉትን ጊዜ በስፋት የሚዳስስ ሲሆን ለታሪክ ማጣቀሻ ሊሆን በሚችል መልኩ ልጃቸው ግርማቸው ተክለሐዋርያት አዘጋጅተው አሳትመውታል።

ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት የማያልፈውን ስራዎቻቸውን ትተውልን በ1969 ዓ.ም. አረፉ፡፡

ተጨማሪ፥ "ፊታውራሪ ተክለሃዋርያት ተክለማርያም - ኦቶባዮግራፊ"
አዲስ አበባ ዩኖቨርሲቲ ፕሬስ 1988ዓ.ም
የመጽሐፍ ግምገማ ኩችዬ kuchiye@gmail.com
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com