ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ተሾመ ነጋሽ ካሣዬ
የደራሲው ሥራዎች
1.   እስከማድረስ?(ልብወለድ)
2.   ጋብቻና የትዳር ሕይወት(ትምህርት)
3.   ይፈለግ መሪ(ትምህርት)
4.   እንዲህ ቢሆን ኖሮ(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ተሾመ ነጋሽ በቀድሞው አርሲ ክ/ሀገር የካቲት ፲፭ ቀን ፲፱፵፬ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርሲ በቆጂ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በራስ ዳርጌ ትምህርት ቤት ተከታትለው አጠናቅቀዋል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የወሰዱ ሲሆን በሥራ አመራር ማስተር ኦፍ ቢዝነስ አድሚንስትሬሽን፤ ኤም.ቢ.ኤ፣ በድርጅታዊ ሥራ አመራር፤ ኦርጋናይዜሽናል ሊደር ሺፕ፣ በሥነ መለኮት የባችለር ዲግሪ አላቸው፡፡

ተሾመ ነጋሽ “እስከማድረስ?”፣ ቅጽ 1 እና 2፣ “ጋብቻና የትዳር ሕይወት”፣ “ይፈለግ መሪ”፣ “እንዲህ ቢሆን ኖሮ”፣ የተሰኙ መጻሕትን ለአንባቢያን አቅርበዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com