ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ሙሉጌታ ጉደታ አድማሱ
የደራሲው ሥራዎች
1.   የተቀጠፈች ጽጌረዳ(ልብወለድ)
2.   የተከፋፈለ ልብ(ልብወለድ)
3.   ሰውና እስስት(ልብወለድ)
4.   ሕልመኛው(ልብወለድ)
5.   The Chillren of Poverty(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ሙሉጌታ ጉደታ መስከረም ፳፫ ቀን ፲፱፵፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመድኃኔዓለም ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሊሴ ገ/ማርያም ተምረዋል። የከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት በዲግሪ ተመርቀዋል፡፡

ሙሉጌታ ጉደታ “የአራዳ ልጆች”፣ “የተቀጠፈች ጽጌረዳ”፣ “የዕንባ ጠብታዎች”፣ “የተከፋፈለ ልብ”፣ “ጭምብል”፣ “ሰውና እስስት”፣ “ሞገደኛው”፣ “ሕልመኛው”፣ “ስደተኛው ፍቅር”፣ የተባሉ መተሕፍትን በአማርኛ፤ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ደግሞ “The Chillren of Poverty” የተሰኙ ልቦለዶችን አሳትመው ለንባብ አብቅተዋል፡፡ ከዚህ ተጨማሪም የእንግሊዝኛ/ አማርኛ መዝገበ ቃላት፣ የአማርኛ ዘይቤዎች መዝገበ ቃላት፣ የእንግሊዝኛ/ ፈረንሳይኛ ቋንቋ መማሪያ፣ ተግባራዊ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ፣ በሚሉ ርዕሶች የተዘጋጁ መጻሕፍትን አሳትመዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com