ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
undefined ነሲቡ ስብሐት Nesibu Sibehat
የደራሲው ሥራዎች
1.   ፍጹም ነው እምነቴ ቀይ ሽብር የከፍተኛ 15 እውነተኛ ታሪክ(ታሪክ)

ስለደራሲው በጥቂቱ

አቶ ነሲቡ ስብሐት መስከረም 2007 ዓ.ም ማለትም September 2015 “ፍፁም ነው እምነቴ የከፍተኛ 15 (ካዛንችስና አካባቢው) ቀይ ሽብር እውነተኛ ታሪክ” መጽሐፍ በመድረስ አስነብበውናል።

አቶ ነሲቡ በትምህርት ደረጃቸው ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1977 ዓ.ም. በፊዚክስ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን አግኝተዋል። በማስከተል The Netherlands ITC Unversity በ1987 ዓ.ም. በጂኦፊዚክስ የማስተር ድግሪያቸውን አግኝተዋል።

ከ1978 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ጂዮሎጂካል ጥናት በጂኦፊዝስትነት ተቀጥረው ሀገራቸውን ለቀው እስከወጡበት እስከ 1995 ዓ.ም. ድረስ አገልግለዋል።

አቶ ነሲቡ ስብሐት ወደ አሜሪካም ከመጡበት 2003 ጀምሮ በNorth American Exploration Virginia Geophyasics Inc. ለአለፉት 12 ዓመት በጂኦፊዝስትነት አገልግለዋል አሁንም እያገለገሉ ይገኛሉ።

በፖለቲካውም ረገድ የተለያዩ አጫጭር ወቅታዊ ጽሁፎችን በማስነበብ ሲታወቁ በተለይ ከ2012 ጀምሮ “ያ ትውልድ ተቋም”ን በመመሥረት ከአጋር ጓደኞቻቸው ጋር የቀይ ሽብር ሰማዕታትን በመዘከርና ለነዚሁ ሰማዕታት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ www.yatewlid.com , www.yatewlid.org ድረ ገጽን በመረጃ ማሰባሰቢያነት ያበረከቱ ናቸው።

አቶ ነሲቡ ከታህሳስ 1970 እስከ ህዳር 1971 ዓ.ም. ያሳለፉትን የከፍተኛ 15 እስር ቤት ሕይወታቸውንና በ1960ዎቹ መጨረሻ እስከ ቀይ ሽብር ዘመን የነበረውን የዚያን ዘመን እውነተኛ የኢሕአፓ ትግል ታሪክ የሚያውቁትን በ2007 ዓ.ም. አስነብበውናል። አቶ ነሲቡ ስብሐት እዚህ አሜሪካም ከመጡ ወዲህ በዴንቨር ኮሎራዶ ስሙንና ማንነቱን ቀይሮ ይኖር የነበረውን የከፍተኛ 15 ቀይ ሽብር ተሳታፊ ከፈለኝ ዓለሙን ነሐሴ 2004 ዓ.ም. በማስያዙና ለፍርድ በማቅረቡ ሂደት ከሌሎች ወገኖቻቸው ጋር የነበረውን ሁኔታና በዚሁ መጽሐፋቸው አቅርበውታል።

አቶ ነሲቡ ስብሐት የ “አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ” www.ethiopiachen.org መሥራችና የዚሁ ንቅናቄ ሊቀመንበር ናቸው።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com