ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ
[1881 - 1931]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ኢትዮጵያና መተማ(ታሪክ)
2.   ደስታና ክብር(ታሪክ)
3.   ዋዜማ(ታሪክ)
4.   በዕድሜ መሰንበት ሁሉን ለማየት(ታሪክ)
5.   ወዳጄ ልቤ(ልብወለድ)
6.   ዐዲስ አለም(ልብወለድ)
7.   ጥሩ ምንጭ(መልክ፥ ገድልና:ነገረ:መለኮት)
8.   ለልጅ ምክር ላባት መታሰቢያ(ትምህርት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
በመርሐቤቴ ረመሸት ቀበሌ ደን አቦ በሚባል አካባቢ የተወለዱት ኀሩይ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያሳዩት በነበረው ትጋትና ቅልጥፍና ፀሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ቀድሞ ይጠሩበት የነበረውን ገብረመስቀልን በመቀየር ኀሩይ አሏቸው።

ለዓፄ ኃይለሥላሴ የቅርብ አማካሪ በመሆን የሃይማኖትና የአስተዳደር ሕጎች እየተረጎሙና የአርትኦት ሥራዎቻቸውን እያጠናቀቁ እንዲወጡ ያደረጉት ብላቴን ጌታ ኀሩይ ታሪክ፣ ማኀበራዊ ጉዳይንና ፍልስፍናን ያካተቱ 42 የሚደርሱ መጻሕፍትን አሳትመዋል፡፡ ከሥራዎቻቸው መካከል “ወዳጄ ልቤ” የሚባለው መጽሐፍ ታዋቂነትንና ተወዳጅነትን አትርፎላቸዋል።

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን መሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው ካሌንደር።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com