ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ተክለጻድቅ መኩሪያ
[1906 - 1992]
የደራሲው ሥራዎች
1.   የግራኝ አሕመድ ወረራ(ታሪክ)
2.   ዐፄ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ አንድነት(ታሪክ)
3.   ዐፄ ዮሐንስና የኢትዮጵያ አንድነት(ታሪክ)
4.   ዐፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት(ታሪክ)
5.   የኢትዮጵያ ታሪክ ኑቢያ [ሜርዌ - ናፖታ] ቅጽ ፩(ታሪክ)
6.   የኢትዮጵያ ታሪክ አኲሱም - ዛጕዬ ቅጽ ፩(ታሪክ)
7.   የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ይኵኖ አምላክ እስከ ዐፄ ልብነ ድንግል ቅጽ፫(ታሪክ)
8.   የኢትዮጵያ ታሪክ ካዐፄ ልብነድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ ቅጽ ፬(ታሪክ)
9.   የኢትዮጵያ ታሪክ ካዐፄ ልብነድንግል እስከ ቀ.ኃ.ሥ ቅጽ ፭(ታሪክ)
10.   ጥንታዊት ኢትዮጵያና ግብፅ(ታሪክ)
11.   ከጣኦት አምልኮ እስከ ክርስትና (ታሪክ)
12.   የሕይወቴ ታሪክ(ታሪክ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ተክለጻድቅ: መኩሪያ: ባ፲፱፻፮: ዓ.ም. : በተጉለትና: ቡልጋ: አውራጃ: አሳግርት: ልዩ: ስሙ: ሣር: አምባ: በተባለ: ሥፍራ: ተወለዱ።

ዕድሜያቸው: ለትምህርት: ሲደርስ: መዠመሪያ: ካ’ባታቸውና: ቀጥሎም: ባ’ጥቢያቸው: ባህላዊውን: ትምህርት: እስከ: ቅኔ: ያለውን: ቀስመዋል።

ከዚያም: ዐዲስ: አበባ: መጥተው: አሊያንስ: ፍራንሴዝና: ከተፈሪ: መኮንን: ት/ቤት: ገብተው: የጊዜውን: የትምህርት: ደረጃ: አጠናቀቅዋል።

ኢጣሊያ: አገራችንን: የወረረች: ጊዜም: በየካቲት: ፲፪: ቀን: ፲፱፻፳፱: ዓ.ም.: ፍጅት: ተይዘው: ወደ: ሶማሊያ: ደናኔ: ተግዘው: ለሦስት: ዓመታት: ታሥረዋል።

ከነጻነትም: መልስ: አገራቸውን: በተለያዩ: የኃላፊነት: ደረጃዎች: አገልግለዋል። መዠመሪያ: ተቀጥረው: ያገለገሉት: በትምህርትና: ሥነጥበብ: ሚኒስቴር: ነበር። እዚያም: እያሉ: ባነራችን: ሰው: የተጻፈ: የአገራችን: ታሪክ: አንድም: ባለመኖሩ: በቁጭትና: በመቆርቆር: ነበር: ‘መጻፍ: አለብኝ’: ብለው: በደንብ: ከሚታወቀው: ከቅርቡ: ጊዜ: በቅጡ: ወደማይታወቀው: የሩቁ: ዘመን: መጣፍ: የዠመሩት።: የመዠመሪያውን: መጽሐፍ: “የኢትዮጵያ: ታሪክ: ከዐፄ: ቴዎድሮስ: እስከ: ቀ.ኃ.ሥ.”: ባ፲፱፻፴፰: ዓ.ም.: አሳተሙ። ከጫፍ: እስከጫፍ: ጽፈው: የመጨረሻውን: መጣፍ: የታሪካችን: መዠመሪያ: የሚኾነውን: የኢትዮጵየ: ታሪክ: ኑብያ - አክሱም - ዛጉዬ: እስከ: ዐፄ: ይኩኖ: አምላክ: ዘመነ - መንግሥት: የሚለውን: ባ፱፻፶፩: ዓ.ም.: አቅርበዋል። እንህኑ: መጻሕፍት: ትምህርት: ሚኒስቴር: ታሪክ: ለማስተማሪያ: በትምህርት: ቤት: ተጠቅሞባቸዋል።

ተክለጻድቅ: ከታሪክ: ውጭ: የጻፉዋቸው: “የሰው: ጠባይና: ዐብሮ: የመኖር: ዘዴና: በሚዮቶሎዢያ: ላይ: ያተኮረ: ከጣዖት: አምልኮ: እስከ: ክርስትና”: የሚሉም: መጣፎች: አሏቸው።

ተክለተድቅ: በምድር: ባቡር: በዋና: ጸሐፊነት: በቤተመጽሐፍት: ወመዘክር: ዋና: ሥራ: አስኪያጅነት፤ እንዲሁም: በፈረንሣይ፣ በእስራኤል፣ በዩጎዝላቪያ: በዲፕሎማሲ: ሥራ: በመጨረሻም: የትምህርትና: የባህል: ሚኒስትር: ኾነው: አግልግለዋል። በፈቃዳቸው: ጡረታ: ከወጡም: በኋላ: በምርምር: የታገኑ: ሦስት: ታላላቅ: የታሪክ: ሥራዎችን: አቅርበዋል።

ተክለጻድቅ: ከረዥም: ያገልግሎት: ዘመን: በኋላ: በተወለዱ: በ፹፮: ዓመታቸው: ሐምሌ: ፲፮ቀን: ባ፲፱፻፺፪: ዓ.ም.: ዐርፈዋል።

ምንጭ: ያሠርቱ: ምእት ፥ የብርእ: ምርት: ከ፲፻: እስከ: ፳፻: ድርሰት: ክፍል: ፩
ዻጉሜ: ፫: ቀን: ፲፱፻፺፱: ዓ.ም: በብርሃነመስቀል: ደጀኔ እና ጌታሁን: ሽብሩ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com