ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ጳውሎስ ኞኞ
[1926 - 1984]
የደራሲው ሥራዎች
1.   አጤ ምኒልክ (ታሪክ)
2.   አጤ ቴዎድሮስ(ታሪክ)
3.   የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት(ታሪክ)
4.   የአራዳው ታደሰ(ልብወለድ)
5.   የጌታቸው ሚስቶች(ልብወለድ)
6.   እውቀት(ፍልስፍና)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ጳውሎስ ኞኞ ኀዳር ፲፩ ቀን በ፲፱፳፮ ዓ.ም. ቁልቢ አካባቢ ተወለዱ፡፡ ጳውሎስ ባጋጠማቸው ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ከአራተኛ ክፍል በላይ ለመቀጠል አልቻሉም ነበር።

ብልህ አእምሮና የፈጠራ ችሎታ ስለነበራቸው በልጅነታቸው የኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች ጣሊያንን ሲገድሉ ወይንም ሲማርኩ ሥዕል በመሣል ያሳዩ ነበር፡፡ ጳውሎስ ካላቸው የጽሑፍ ፍቅር የተነሣ የ “ድምፅ ጋዜጣ” አዘጋጅ በመሆን የብዕር ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡ ጋዜጦች ላይ ከጽሑፍ አቅራቢነት አስከ አዘጋጅነት ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል፡፡ በተለይ “አንድ ጥያቄ አለኝ” በሚለው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይወጣ በነበረው ዓምድ በሚሰጡት መልስ ታዋቂነትን አግኝተዋል፡፡ ጳውሎስ ብዙ መጻሕፍትን ጽፈዋል፡፡

ጳውሎስ ከ፲፱፶፭ ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ዕድገት የነበራቸው ተሰጥኦ በአግባቡ በሥራ ላይ ያዋሉ ዕውቅ ጋዜጠኛና ደራሲ ነበሩ፡፡

ምንጭ: የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com