ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ገብረሕይወት ባይከዳኝ
[1879 - 1912]
የደራሲው ሥራዎች
1.   ዐፄ ምኒልክና ኢትዮጵያ(ታሪክ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ በ1879 ዓ.ም. በአድዋ አካባቢ ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ኤርትራ ውስጥ በሚገኘው የሲዊድን ሚሽን ከተማሩ በኋላ ወደ ጀርመንና አውስትራሊያ በመሄድ የሕክምና ትምህርታቸውን አጠናቀቁ፡፡ ከጀርመን ሚሽን ጋር ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ በዓፄ ምኒልክ ቤተመንግሥት ፀሐፊ በመሆን ሠርተዋል። የምኒልክ ሐኪም ለነበረው ጀርመናዊ ዶክተር አስተርጓሚ ሆነው ሲያገለግሉ ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በነበራቸው አለመግባባት አገር ለቀው ወደ ሱዳን ተሠደዱ፡፡ ከዛም ለሱዳን መንግሥት የሀገር ውስጥ ደኀንነት ሲሠሩ ቆይተው ወደሀገራቸው በመመለስ በቤተመንግሥት ውስጥ ማገልገል ጀመሩ፡፡ በመቀጠልም የድሬዳዋ ጉምሩክ ኃላፊ ሆነው ተመድበው በራስ ተፈሪና በሌሎች ተቀናቃኞች ወገኖች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ራስ ተፈሪን ወግነሀል በሚል ከኃላነታቸው ተነሱ፡፡

እኝህ የኢኮኖሚ ፈላስፋና የሕክምና ምሁር በ1912 ዓ.ም. በኀዳር በሽታ ሕይወታቸው ቢያልፍም “መንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር” በሚለው ዝነኛ መጽሐፋቸው የሀገሪቱን የውስጥ ጉዳይ አስተዳደርና ኢኮኖሚ እንዲሁም በትምህርት ላይ ፍጹም ለውጥ እንዲኖር አሳስበዋል፡፡ መጽሐፋቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው በአቶ ጳውሎስ ኞኞ አማካይነት ነው፡፡
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com