ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ቀኝ/አ ያሬድ ገብረ ሚካኤል
የደራሲው ሥራዎች
1.   ስለእንሰሳት አገልግሎት ፥ ለሕጻናት በረከት(ትምህርት)
2.   ይምጡ በዝና ወዳዲስ አበባ(ታሪክ)
3.   ግርማዊት እቴጌ መነን(ታሪክ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ቀኝ/አ ያሬድ ገብረሚካኤል ለስድስተኛው የግርማዊት እቴጌ መነን አስፋው የልደት መታሰቢያ በ፲፱፶ ዓ.ም.፣ “ግርማዊት እቴጌ መነን” በሚል ርዕስ መጽሐፍ አሳትመዋል። ስለእሳቸው ታሪክ ሙሉ መረጃ ባይገኝም በዚሁ ባሳተሙት መጽሐፍ ውስጥ ዕድገታቸው የትእንደነበር የሚጠቁም ሀሳብ ሰፍሯል፡፡ “. . . በመታደል በቤተ መንግሥትዎ ቅፅር ግቢ በመንበር ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ዘኒጋባ ሆኜ ትምህርቴን እየቀጠልሁ በምኖርበት ጊዜ . . .” በማለታቸው ዕድገታቸው ቤተመንግሥት አካባቢ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በተጨማሪም ስለ እንስሳት አገልግሎት ለሕፃናት በረከት የሚል ለማስተማሪያ ያገለገለ የግጥም መጽሐፍ ጽፈዋል፡፡

በእቴጌይቱ የሕይወት ታሪክ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ውስጥ ደራሲው ከ0928 ዓ.ም. በፊት የነበሩበትን ሁኔታ ለማስታወስ የተነሱት ፎቶ ይህ ነው፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com