ተክለ ጻድቅ በፀሐፊነታቸው ግዙፍ ሰው ቢሆኑም፣ስብእናቸው እና ፖለቲካዊ አስተያየታቸው በአደባባይ እምብዛም የሚታወቅ አልነበረም። ይህ መጽሐፍ የበለጠ እንድናውቃቸው ፣ እንድንተቻቸው ወይም እንድናደንቃቸው ብሎም እንድናከብራቸው የሚጋብዙንን ብዙ ቁም ነገሮች አዝሏል። የደራሲውን ስብእና ፣ የሕይወት ገጠመኞችና ፖለቲካዊ ሚና በቅንነትና በድፍረት ያቀርብልናል። ድርሰቱ ብልህነትንና ፈሊጥነትን አጣምሮ ግልፀኝነትን ተንተርሶ ማንም አንባቢ በቀላሉ ሊረዳው በሚችል ቋንቋ ተጸፏል።
ገብሩ ታረቅ
የታሪክ ኢመሬት ፕሮፌሰር
በብሔራዊ ቴያትር የመጽሐፉ ምረቃ ስነሥርዐት ላይ የተገኙ እንግዶች ያደረጉት ንግግር፦
- የፕሮግራሙ መሪ ተፈሪ አለሙ እና ልጃቸው የዓለምእሸት ከበደ ያደረጉት የመግቢያ ንግግር።
- ሪታ ፓንክረስት Rita Pankhurst (a memoir) ያደረጉት ንግግር።
Part I |
Part II
- ጌትነት እንየው፣ ዘነበ ኦላ፣ አስፋው ዳምጤ፣ በመጨረሻም ደጃዝማች ወልደሰማያት ገብረወልድ መጽሐፉን ሲመርቁ ያደረጉት ንግግር።