የኢትዮዽያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
 
     


የኢትዮጵያና የጣልያን ሁለተኛው ጦርነት ታሪክ ደራሲ:(ጥላሁን ጣሰው)
 
ቀዳሚ ቃል በአቶ አበራ ሞልቶት

ደራሲትላሁን ጣሰው 'የኢትዮጵያና የጣልያን ሁለተኛው ጦርነት ታሪክ' በሚል ርዕስ ከ1928 የግፍ ወረራ እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ የተካሄደው የጣሊያንና የኢትዮጵያ ጦርነት አነሳስና አፈጻጸም የሚገልጥ የታሪክ ትንታኔ አቅርቦልናል።

ደራሲው በመግቢያው ላይ እንዳቀረበልን ጽሑፉን ያቀረበው የጦርነቱን ሂደት እንደወረደ በማተት ሳይሆን አላማውን ፣ እቅዱን ፣ አፈጻጸሙን ፣ በመመርመር ፣ በመገምገምና በመተንተን እንደሆነ ይነግረናል። የተባለውም እውነትነት በንባበባችን በግልጥ ይታያል።

በብዙ ቦታ ይህ የሙሶሎኒ የ1928 ዓ.ም ቀረራ በበርካታ ደራሲአየን የማይጨው ጦርነት እየተባለ ስለሚጠራ አቶ ትላሁን ጣሰው የሰጠው ርእስ ተመራጭ እንደሚሆን አያጠራጥርም።

በንባባችን ስንቀጥል ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው የአለም ጦርነት መጨረሻ በኋላ የነበረችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ እንገነዘባለን። ኢትዮጰይ በጊዜው የነበረው የዓለም መንግስታት ማኅበር አባል በመሆኗ ለነፃነቷ ጥበቃ የማኅበሩን ድጋፍ ማግኘት የሚገባት ቢሆንም ይልቁንም ከማዘናጋት ያለፈ ምንም ያገኝቸው ነገር የለም።

ጣልያን ከአድዋ ድል መኋላ ለበቀልና ለወረራ እርምጃ በሙሉ ኃይሏ የጦር ሰራዊቷን ስታጠናክር የጋዝመርዝ ሳይቀር ይዛ ትጥቋን እስካፍንጫዋ ስታዘጋጅ በኢትዮጵያ በኩል በዚህ ረገድ የተወሰደ ምንም እርምጃ አልነበረም። በቅን ገዢ ጎረቤቶቿ በፈረንሳይ በእንግሊዝና በጣሊያን በነበረባት የተቀነባበረ ጭቆና ምክንያት የምትፈልገውን የጦር መሳሪያ ከውጪ ገዝታ ማስገባት እንኳን አልቻለችም ነበር።

ኢትዮጵያ በነበረችበት በዚህ ዓይነት የተዳከመ ሁኔታ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ገና ከመጀመሪያው አዲስ የሆነ የዐውደ ውጊያ ጦርነትና የተራዘመ ጦርነት ስልቶች የተቀናጁበት በአርበኛ ሰራዊት አመራር በመተግበር ወረራውን ለመቀልበስ በተከተሉት መንገድ በ1953 ዓ.ም የኢትዮጵያ ነፃነቷን ለመቀዳጀት መቻሏን ከንባባችን እንረዳለን። ይህ ከጦርነቱ መነሻ ጀምሮ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የተከተሉት ሰትራተጂ መጀመሪያ ላይ በትልልቅ ግንባሮች መልሶ ማጥቃት ከመደረጉ በፊት እያጠቁ በማፈግፈግ ሲተገበር በሰሜን፣ በኦጋዴንና ደቡብ የጦር ግንባሮች እናያለን። ከማይጨው ጦርነት በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ዋና ከተማቸው ገብተው መንግስቱ ወደ ጎሬ ተዘዋውሮ እዲሠራ ፣ አርበኛው በየግምባሩ የመከላከል ጦርነትን እንዲቀትል ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ተስፋ ባለመቁረጥ ኢትዮጵያ በዓለም መንግሥታት አባልነቷ የሚገባትን ዕርዳታ በግምባር ሆነው እዲጠይቁ ወደ ኤሮፓ እንዲሄዱ ከተወሰነም በኋላ ገጠርን ማእከሉ ያደረገው አርበኛ ሰራዊት ጠላትን በካምፕና በከተሞች ውስት ከቦ ሲንቀሳቀስ እያጠቁ በመመለስና በመጨረሻም ንጉሠ ነገሥቱ ወደ አገር ቤት ሲመለሱ ከትልልቅ የግንባር ጦርነቶች ጋር ተቀናጅቶ ለውጤት ሲበቃ እናያለን።

አንዳንድ ሰዎች የንጉሠ ነገሥቱን ወደ ኤሮፓ መሄድ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ አንደ ሽሽት ይቆጥሩታል። አቶ ትላሁን በዚሕ መጽሐፉ የጉዞውን አላማና አስፈላጊነት ጥርት አድርጎ ይነግረናል። የጣሊያኖች ዋናው ምኞት ንጉሠ ነገሥቱን ከሕዝቡ ተጥሎ ማስቀረት ፣ መግደል ወይም መማረክ አንደሆነ ያመለክታል። የንጉሠ ነገሥቱ በውጪ መሆን ከጣልያኖች በፖለቲካና በጦር አቅጣጫ ለመዋጋት አስፈላጊነቱን ያሳየናል። ንጉሠ ነገሥቱ ያደረጉት የፖለቲካ ትግል፣ ጣልያን ሕዝብ በብዛት የሰፈረባቸውን አንዳንድ ትልልቅ ከተሞችን ከመያዛ በስተቀር አገሪቷ አሁንም ቢሆን በአርበኞቻቸው ቂጥጥር ሥር መሆኗን በመረጃ በተደገፈ ሪፖርት ለመንግስታት ማኅበሩና ለመላው የዓለም ሕዝብ ላማስታወቅ አስችሏል። በሌላው በኩል በጦር ግምባሩም ቢሆን ንጉሠ ነገሥቱ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ከአርበኞች አልተለዩም። መልእክተኞቻቸውን ሳያቋርጡ ወደ ሀገር ቤት በመላክ ከትልልቆቹ አርበኞች ግንኙነት ማድረጋቸውና አመራርና ድጋፍ መስጠታቸው የማይካድ እውነት ነው። ይህም የመጨረሻው ድል ዋነው አካል ነው።

የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ ከእንግሊዝ ሠራዊት ጋር በመተባበር የራሳቸውን ጦር ይዘው ጠላትን እየደመሰሱ በጎጃም በኩል ዋናው ከተማቸው አዲስ አበባ ሚያዚያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም መግባታቸው የኢትዮጵያ ዕውነተኛ ትንሳኤ እንደሆነ ከንባባችን እንረዳለን።

ሌላው ትልቁ ጉዳይ ደራሲ ጥላሁን ጥርት ባለ ቋንቋ ይህ ከአምስት አመት በላይ የፈጀ ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበት ያላቋረጥ ትግል ለድል የበቃው በንጉሰ ነገሥቱ መሪነት፣ በተጋዳይ አርበኞች ቆራጥ ትግል፣ በስደት ታጋዮችና በውስት አርበኞች መስዋዕትነት፣ በመላው ሕዝብ ታማኝነትና ድጋፍ ከእንግሊዞች በተገኘው ከፍተኛ የአየርና የምድር ጦር ዘመቻ መሆኑ ነው። የነፃነት ትግል ጣልያኖችን ድል አድርጎ በማስወጣት ብቻ ያልተወሰነና ከእንግሊዝ ጦር አገዛዝ ለመከላከል የተደረገው ትግል ታላቅ ትእግስትን ጥበብን የጠየቀ መሆኑን ደራሲው አስገንዝቦናል።

በማንኛውም ስለ ።ሁለተኛው የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት ታሪክ ' ጠቅላላ እውቀት ለማግኘት ለሚፈልጉ፣ ለከፍተኛ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወይም ስለኢትዮጵያ ወደፊት ጥልቅ ምርምር ለሚያደርጉ ሰዎች የመጽሐፉን ጠቃሚነት ለማረጋገጥ እወዳለሁ። አቶ ጥላሁን ጣሰው በዚህ አስተዋጽዖው ባለውለታችን ነው።

 
 
 
 
ስለመጽሐፉ የአንባብያን አስተያየት።       

መጽሐፉን አንብበውት ከሆነ ስለመጽሐፉ ያለዎትን አስተያየት ይጻፉ።
If you have already read the book, please write your review or comment.

ስም /Name: *
ኢሜይል /Email: *
አስተያየት/
Your book review:
*
   
Dear Readers: The views expressed on our comment section below are the personal views of individual contributors and ethireaders.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that Comments are moderated if necessory.
 
 
 
 
   
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com