የኢትዮዽያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
 
     


የአቶሚክ ኢነርጂ ታሪክ ደራሲ:(ይልማ ወረደ)
 
ይህ መጽሐፍ የሳይንስ ፍቅር ላላቸው ብቻ አይደለም። ማንኛውም አንባቢ ቢያነበው በቀላሉ ሊረዳው በሚችል ቀለል ባለ አማርኛ ቋንቋ የተጻፈ ነው። መጽሐፉን ማንበብ ስለ አቶሚክ ኢነርጂ መሰረታዊ የሆነውን እውቀት ያስጨብጣል። ታሪኩ የአቶሚክ ኢነርጂን ግኝት ከአጀማመሩ እስካሁን መጽሐፉ እስከተጻፈበት ጊዜ ድረስ ያለፈበትን ውጣ ውረድና በአሁኑ ጊዜ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ያስረዳናል። መጽሐፉ ለአቶሚክ ኢነርጂ መገኘት ከፍተኛውን አስተዋጽዎ ያበረከቱትን ተመራማሪዎች የቅብብሎሽ የሥራ ውጤት እንዲሁም የህይወት ጉዞን ይዳስሳል። ከዚህ ታሪክ ውስጥ የሁለት ጊዜ ኖቤል ተሸላሚዋ የፖላንዶ ሜሪ ኩሪ እና የባለቤቷ ፒየር የህይወት ታሪክን ስናነብ እጅግ እንመሰጣለን። የሽማግሌው ኒልስ ቦር፣ የወጣቱ ረዳት ተመራማሪ እንዲሁም የመጀመሪያውን የአቶሚክ ኤነርጂ የማመንጨት ሙከራውን በተሳካ መንገድ ሎስ አላሞስ ላይ በሐላፊነት የመራው በትውልድ ጣሊያናዊ የሆነው የኤነሪኮ ፈርሚን ታሪክ እናገኛለን። ፈርሚን ተመራማሪዎቹ የአቶሚክ ኢነርጂ አባት ይሉታል። የአቶሚክ ኤነርጂው ምርምር እንዲቀጥል ወደአሜሪካ ተሰዶ በነበረበት ጊዜ ያደረጋቸው ከፍተኛ አስተዋጽዎች ለማንኛውም አንባቢ ትምህር ሰጪና አስተማሪ ናቸው። ብዙዎቻችን የአቶሚክ ኤነርጂ ግኝትን ከታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ጋር እናቆራኘዋለን ከዚህ መጽሐፍ የአልበርታንስታይንን ለአቶሚክ ኢነርጂ መገኘት ያበረከተውን ትክክለኛ አስተዋጽዎ ምን እንደነበር እናነባለን። ይህን መጽሐፍ ወጣት ተማሪዎች ሊያነቡት ይገባል፤ ምክንያቱም እንዲህ ነው ያለጥርጥር ልባቸውን ለሳይንስ ፍቅር ይከፍተዋልና። መቼም አንዴ ማንበብ ከጀመሩት የማያስቀምጡት፣ከተቀመጡበት በአንድ ትንፋሽ ካልጨረሱ ብድግ የማይሉበት መጽሐፍ ነው።
 
 
 
 
ስለመጽሐፉ የአንባብያን አስተያየት።       

መጽሐፉን አንብበውት ከሆነ ስለመጽሐፉ ያለዎትን አስተያየት ይጻፉ።
If you have already read the book, please write your review or comment.

ስም /Name: *
ኢሜይል /Email: *
አስተያየት/
Your book review:
*
   
Dear Readers: The views expressed on our comment section below are the personal views of individual contributors and ethireaders.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that Comments are moderated if necessory.
 
 
 
 
   
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com