[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
የኢትዮጵያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
አ
በ
ቨ
ገ
ደ
ጀ
ሀ
ወ
ዘ
ዠ
ሐ
ኀ
ጠ
ጨ
የ
ከ
ኸ
ለ
መ
ነ
ኘ
ሠ
ዐ
ፈ
ጸ
ፀ
ቀ
ረ
ሰ
ሸ
ተ
ቸ
ጰ
ፐ
ወደ ዋና ገጽ
አሐዱ ሳቡሬ Ahadu Sabure
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1674 - 1699]
ዐፄ አድያም ሰገድ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1930 - 1990]
ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ Pro. Ashenafi Kebede
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አሕመዲን ጀበል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አሰፋ ጫቦ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አሳምነው ገብረወልድ Asamnew Gebrewold
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አቤ ጉበኛ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አቤ ጉበኛ በ፲፱፳፭ ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ ተወለዱ፡፡ በስድስት ዓመታቸው ፊደል ቆጥረው ንባብ ተማሩ፡፡ ቀጥሎም የቤተክርስቲያን ትምህርት ተከታተሉ፡፡ ከዚያም ወደ ዳንግላ ሄደው ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ተብሎ ይጠራ በነበረ ትምህርት ቤት እስከ ስድስተኛ ክፍል ተማሩ። ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀቁ፡፡
አቤ ጉበኛ በመጀመሪያ ሥራ የጀመሩት ማስታወቂያ ማኒስቴር ቀጥሎ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ሲሆን በመንግሥት ሥራ ከስድስት ዓመት የበለጠ አልቆዩም፡፡ ሕይወታቸውን በአብዛኛው የገፉት በደራሲነት ነው፡፡ አቤ ጉበኛ ለትውልድ ቅርስ የሚሆኑ የተለያዩ ድርሰቶችን በአማርኛና በእንግሊዝኛ በመድረስ አባትመዋል፡፡ ካሳተሟቸው በርካታ መጽሐፎች በተጨማሪ “ቂመኛው ባሕታዊ” እና የ “ደካሞች ወጥመድ” የተባሉ ቲያትሮች አዘጋጅተው ለሕዝብ ታይተዋል፡፡
በአቤ ጉበኛ ብዕር ተከሽኖ የቀረበና በ፲፱፷፮ ዓ.ም. ዳግም ለኀትመት የበቃው እና አብዮቱ በሀገሪቱ ሲቀጣጠል በኀብረተሰቡ ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ የተነበበው “አልወለድም” የተሰኘው መጽሐፍ ማንም ሰው ከእናቱ ማሕጸን ጀምሮ ምኞትና ጥንቃቄ ሊለየው እንደማይገባ የሚያትት ሲሆን በመታየት ላይ ያለው እውነታ ግን አዳጋች የሆነና የሰው ዘር በድህነት ተወልዶ አድጎና ኑሮው በድህነት እንደሚያልፍ ያሳያል፡፡ እንዲህ ያለው ሁኔታ አግባብ አለመሆኑንም ይቃወማል፡፡
መጽሐፉ የሰው ልጅ የሚደርስበትን መከራ በመቃወም ይሞግታል፡፡ የሰው ልጅ መብት በአግባቡ መጠበቅ እንዳለበትም ያስረዳል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
አቤ ጉበኛ በ፲፱፳፭ ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ ተወለዱ፡፡ በስድስት ዓመታቸው ፊደል ቆጥረው ንባብ ተማሩ፡፡ ቀጥሎም የቤተክርስቲያን ትምህርት ተከታተሉ፡፡ ከዚያም ወደ ዳንግላ ሄደው ቢትወደድ መንገሻ ጀንበሬ ተብሎ ይጠራ በነበረ ትምህርት ቤት እስከ ስድስተኛ ክፍል ተማሩ።
አማረ ማሞ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አማረ ማሞ በ፲፱፴፱ ዓ.ም. በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ፊደል በመቁጠር ዳዊት ደግመዋል፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለው በሥራ ዓለም በቀድሞው የምሥራች ድምፅ ውስጥ የሥነ ጽሑፍ ኃላፊ ሆነው ከማገልገላቸውም በተጨማሪ የትርጉም ሥራዎች ሠርተዋል።
አማረ ማሞ ለረጅም ዓመታት የኢትዮጵያ መጽሐፍት ድርጅት ም/ሥራ አስኪጅ በመሆን አገልግለዋል፡፡ የተለያዩ ድርሰቶችን በመድረስና የትርጉም ሥራዎችን በማዘጋጀት ከሰላሳ በላይ መጻሕፍት አሳትመዋል፡፡ ከ፲፱፷፮ ዓ.ም. በኋላም በርካታ ወይ ድርሰቶችንና የድርሰት መማሪያ መጻሕፍትን ለንባብ አብቅተዋል። ከነዚህም መካከል በ፲፱፷፰ ዓ.ም. "የልብ ወለድ ድርሰት አጻጻፍ"፣ በ፲፱፸፮ ዓ.ም. "የቀለም ጠብታ" እና በ፲፱፹፬ ዓ.ም. "አሳረኛው"፣ በሚል የታተመው የትርጉም ሥራም ተጠቃሾች ናቸው። ለሀገራችን የሥነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ደራስያን ማኀበር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን መህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
አማረ ማሞ በ፲፱፴፱ ዓ.ም. በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ ፊደል በመቁጠር ዳዊት ደግመዋል፡፡ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለው በሥራ ዓለም በቀድሞው የምሥራች ድምፅ ውስጥ የሥነ ጽሑፍ ኃላፊ ሆነው ከማገልገላቸውም በተጨማሪ የትርጉም ሥራዎች ሠርተዋል።
አባ ገብርኤል
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አባ ገብርኤል
አባ ገብርኤል።
[1860 - 1939]
ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ Afework Gebreyesus
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ በ1860 ዓ.ም ጎንደር ዘጌ በተሰኘችው ስፍራ ተወለዱ፡፡ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የሥጋ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው አፈወርቅ በልጅነት ዕድሜያቸው አዲስ አበባ መጥተው አደጉ።
ለዘመናዊት ኢትዮዽያ ሥልጣኔ መስራች የሆኑት ዳግማዊ አጤ ምኒሊክ ያውሮፓን ሥልጣኔ ቀስመው እንዲመጡ ወደውጭ ሀገር ከላኳቸው ብልህ ወጣቶች መካከል አንዱ አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ ናቸው።
አፈወርቅ የ20 ዓመት ብላቴና ሳሉ በአጤ ምኒልክ በጎ ፈቃድ ከሁለት ወጣቶች ልጅ ጉግሳ ዳርጌ እና ልጅ ቅጣው ዛማኑኤል ጋር በ1880 ዓ.ም ወደ ስዊዘርላንድ ተላኩ። ከዚያ ከደረሱ በኋላ በገዛ ፈቃዳቸውና ባልታወቀ ምክንያት ወደ ጣሊያን ቱሪን ሄደው በኮሌጅ ኢንተርናሲዮናል ደ.ቤሊ አርቲ ከፍተኛ የሥነ ጽሑፍ ትምህርት ተከታተሉ። ከአድዋ ጦርነት በ1986 በፊት ወደ ኢትዮዽያ ተመልሰው በ1882 በቤተመንግስት ባለሟልነትና በሠዓሊነት ሙያ ያገለገሉት አፈወርቅ፥ በተለይ ከእቴጌ ጣይቱ ጋር በመቀያየማቸው በ1888 ዓ.ም. በስደት መንፈስ ወደ ኢጣሊያ ተመለሱ። በናፖሊ የምስራቅ ጥናት ኢንስቲቲዩት የአማርኛ ቋንቋ በማስተማር የፕሮፌሰርነት ማእረግ አግኝተዋል።
አፈወርቅ በኢጣሊያ ሳሉ ለኢትዮዽያ ዘመናዊ ሥነ ጽሁፍ ዕድገት የበኩር ልጅ ሊያሰኙዋቸው የቻሉትን የአማርኛ መጻሕፍት የጻፉ ሲሆን እንደገና ወደሀገራቸው በ1922 ዓ.ም. እስከተመለሱ ድረስ፥ በግእዝ፥ በአማርኛ፥ በኢጣሊያንኛ እና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎች የመማሪያ መጻሕፍት፥ የታሪክ እና የፈጠራ ልቦለድ መጻሕፍትን አሳትመዋል።
አፈወርቅ በ1902 ዓ.ም. ሮማ ባሳተሙት ዳግማዊ ምኒሊክ በሚለው የታሪክ መጽሐፋቸው ከግዕዝ ጽሑፍ ባህል ወደ ዘመናዊ አማርኛ ኪናዊ ሥነጽሑፍ ለተደረገው ሽግግር በተለይ በ1908 ዓ.ም. በሮም ባሳተሟት ጦቢያ-ልቦለድ ታሪክ የፈጠራ ሥራቸው-በኢትዮዽያ የአማርኛ ዘመናዊ ሥነጽሑፍ መሥራች ካሰኛቸው ማእረግ ባሻገር በአፍሪካ ቋንቋዎችም ታሪክ- በሀገርኛ ቋንቋ በመጻፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ የሚል ምስክርነት አግኝተዋል።
ቀደም ሲል ለሀገራቸው በአስተርጓሚነት፥ በጉምሩክ ሥራ ኃላፊነት ነጋድራስነት እና በአምባሳደርነት ሮም ያገለገሉት አፈወርቅ በኢትዮዽያና ኢጣሊያን ጦርነት ወቅት 1924 - 1933 ኢጣሊያን ወገን ሆነው በ የቄሣር መንግስት መልእክተኛነት በሀገራቸው ልዩ በደል ፈጽመዋል በሚል ከነፃነት በኋላ በ1933 የዕድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶባቸው በጅማ ጅሬን እሥር ቤት ለ6 ዓመታት በግዞት ቆይተው፥ በእርጅና እና በጤና ማጣት መስከረም 15 ቀን 1939 ዓ.ም በ79 ዓመታቸው አረፉ።
ምንጭ:
ብርሀነመስቀል ደጀኔ 2000ዓ.ም ብራና.ማ.ቤ ካሌንደር።
አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ በ1860 ዓ.ም ጎንደር ዘጌ በተሰኘችው ስፍራ ተወለዱ፡፡ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የሥጋ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው አፈወርቅ በልጅነት ዕድሜያቸው አዲስ አበባ መጥተው አደጉ።
አባ ባሕርይ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አዛዥ ሲኖዳ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አባ ጋስፓሪኒ ገብረማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አስረስ የኔሰው Asrese Yeneneh
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አለምፀሓይ ወዳጆ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አባ ጎርጎርዮስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አምሳሉ አክሊሉ Amsalu Aklilu
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1920 - 1996]
ኑርልኝ አበራ ጀምበሬ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አበራ ጀምበሬ በቀድሞ ሸዋ ክፍለ ሀገር ነሐሴ ፳፯/፲፱፳ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞው ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ገብተው አጠናቅቀዋል። ከዚያም በማስከተል በቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የቤ.ኤ እና የኤል.ኤል.ቢ BA LLB ዲግሪዎቻቸውን ወስደዋል፡፡ አበራ ጀምበሬ “ስለጋብቻችሁ”፣ “የቀ.ኃ.ሥ. በጎ አድራጎት ድርጅት መመሥረት”፣ “አባ ኮስትር”፣ “ብቸኛው ሰው”፣ “አባ ገስጥ”፣ “የእሥር ቤቱ አበሳ” በሚሉ ርዕሶች መጻሕፍት አሳትመው ለአንባቢያን ያበረከቱ ሲሆን ገና ያልታተሙ ሥራዎችም አሏቸው፡፡
አበራ ጀምበሬ በቀድሞ ሸዋ ክፍለ ሀገር ነሐሴ ፳፯/፲፱፳ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞው ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ገብተው አጠናቅቀዋል።
አንዳርጋቸው አሰግድ Andargachew Asegid
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አርአያ ሙሉጌታ Araya Mulugeta
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተሰማ አጥናፍሰገድ ይልማ Atinafe Yilama
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አጥናፍሰገድ ይልማ በቀድሞው አርሲ ክ/ሀገር ልዩ ስሙ “ጥቾ” በተባለ ቦታ ግንቦት ፳፯ ቀን ፲፱፳፱ ዓ.ም. ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ቀ.ኃ.ሥ. ጢቾ ትምህርት ቤት በ፲፱፵፰ ዓ.ም. አጠናቀቁ፡፡ ከዚያም በ፲፱፶፩ ዓ.ም. አዲስ አበባ ንግድ ሥራ ት/ቤት ገብተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ፈጸሙ፡፡ በፖለቲካል ሳይንስና ሥነ መንግሥት ተጨማሪ ዕውቀት ገብይተዋል፡፡ አጥናፍሰገድ ይልማ “የበደል ካሳ” በሚል ርዕስ ታሪካዊ ልቦለድ መጽሐፍ አሳትመው ለአንባቢያን አቅርበዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
አጥናፍሰገድ ይልማ በቀድሞው አርሲ ክ/ሀገር ልዩ ስሙ “ጥቾ” በተባለ ቦታ ግንቦት ፳፯ ቀን ፲፱፳፱ ዓ.ም. ተወለዱ።
አቢይ አበበ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አማረ አፈለ ብሻው
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አገኘሁ እንግዳ Agegnehu Engida
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አስረስ አስፋወሰን Asrese Asfawosen
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1912 - 1961]
አሰፋ ገብረማርያም ተሰማ Asefa Gebremariam Tesema
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አቶ አሰፋ ገ/ማርያም ተሰማ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርበኞች ት/ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጄኔራል ውንጌት ት/ቤት ተምረዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በቀድሞው ሶቪየት ኀብረት ሌኒን ግራድ ዩኒቨርሲቲና በእንግሊዝ ሀገር በሚገኘው ኢንደንብራ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ሰልጥነዋል፡፡
ለኀትመት የበቁላቸው ሥራዎች "የመስከረም ጮራ"፤ እና “The Voice” የተሰኙ የግጥም መድብሎች ይጠቀሳሉ፡፡ በቲአትር ዘርፍ "ዩሊየስ ቄሳር"፣ "ዋናው ተቆጣጣሪ" የትርጉም ሥራዎች እና "ከለንደን አዲስ አበባ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ወጥ ቲአትር ለመድረክ አብቅተዋል፡፡ የደርግ ዘመንን ብሔራዊ የሕዝብ መዝሙርም ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኀበርን በዋና ፀሐፊነት መርተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
አቶ አሰፋ ገ/ማርያም ተሰማ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርበኞች ት/ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጄኔራል ውንጌት ት/ቤት ተምረዋል።
አማኑኤል መሐሪ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አበበ አይቸህ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አዳም ረታ ብዙነህ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አዳም ረታ ሐምሌ ፰ ቀን ፲፱፵፱ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በባልቻ አባነፍሶ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በልዑል መኮንን ት/ቤት፣ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ ከአ.አ. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ይዘዋል። በጂኦግራፊ ሙያ ልዩ ዘርፍ ሠልጠጥነዋል፡፡ በ፲፱፸፯ ዓ.ም. በታተመው “አባ ደፋርና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች”፣ መድብል ውስጥ አራት አጫጭር ልቦለድ ድርሰቶችን አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም “ማኀሌት”፣ “ግራጫ ቃጭሎች”፣ የሚሉ መጻሕፍትን ለአንባብያን አቅርበዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
አዳም ረታ ሐምሌ ፰ ቀን ፲፱፵፱ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በባልቻ አባነፍሶ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በልዑል መኮንን ት/ቤት፣ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ ከአ.አ. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ይዘዋል።
ኮ/ል አስራት ቦጋለ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ኢብንፈድል አላህ ኣል ዑምሪ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1462 - 1552]
እጨጌ እንባቆም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
እንዳለ ጌታ ከበደ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዶ/ር እግረጸሐይ ፍቅሬ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዑቍባሚካኤል ሀብተማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዓለማየሁ ነሪ ውርጋሶ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዓለማየሁ ነሪ ቀኛዝማች እኖር ማፌድ በተባለ ሥፍራ ሐምሌ ፭ ቀን ፲፱፻፳፮ ዓ.ም. ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአልያንስ ፍራንሴዝና ሱዳን ኢንተሪየር ሚሽን ት/ቤቶች ከተማሩ በኋላ በሽመልስ ሀብቴ ትምህርት ቤት ገብተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል፡፡
ዓለማየሁ ነሪ “ኧሰት” የባህልና የታሪክ መሠረት አንደኛ መጽሐፍ፣ የባለታሪኮች ዳግም ልደት “ኧሰት” ሁለተኛ መጽሐፍ፣ ኢትዮጵያዊ ሲሳይ “ኧሰት” ሦስተኛ መጽሐፍ፣ በተከታታይ አሳትመው ለአንባብያን አቅርበዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ዓለማየሁ ነሪ ቀኛዝማች እኖር ማፌድ በተባለ ሥፍራ ሐምሌ ፭ ቀን ፲፱፻፳፮ ዓ.ም. ተወለዱ።
አባ ዐምደ ሐዋርያት
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዐሥራት ገብረማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ዐጽመ ጊዮርጊስ ገብረመሲሕ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1306 - 1336]
ዐፄ ዐምደጽዮን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መጻሕፍት ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ
ይጫኑ
ተመዝግበው ከሆነ እዚህ
ይጫኑ
[
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ቋንቋ
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
]
[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com