|
|
ጎበዜ ጣፈጠ |
|
|
|
|
|
[1533 - 1503] |
|
ዐፄ ገላውዴዎስ |
|
|
|
|
|
ገብሬ ወዳጆ |
ገብሬ በ፲፱፲፱ ዓ.ም. በመንዝና ግሼ አውራጃ ማማ ምድር ወረዳ እምቢ ጣጣ ቀበሌ ተወለዱ፡፡ ከተወለዱበት አካባቢ በ፲፱፴፫ ዓ.ም. ለቀው አዲስ አበባ መጡ፡፡ መጀመሪያ በዓታ ከዚያም ዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት ገብተው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። ከዛም በብሪቲሽ ካውንስል የሁለት ዓመት ሥልጠና ተከታትለው በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡
በአዲስ አበባና በተለያዩ ክፍላተ ሃገራት ት/ቤቶች በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ተዛውረው ዘመናዊ የመማሪያ መጻሕፍትን አዘጋጅተዋል፡፡
በዚሁም ከመማሪያ መጻሕፍት አዘጋጆች የምሥክር ወረቀት ተሸልመዋል፡፡ እንዲሁም በመሥሪያ ቤቱ ትምህርት ነክ በሆኑ ልዩ ልዩ ክፍሎች እየተዘዋወሩ ሠርተዋል፡፡ ዕውቀትን በማሻሻል በኩል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሕግ ትምህርት ዲፕሎማ ተቀብለዋል፡፡
ገብሬ ወዳጆ ያሳተሟቸውና በ፲፱፵፮ ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት ሚኒስቴር በሥራ ላይ አውሏቸው የነበሩ መጽሐፍት የፊደል መማሪያ፣ የመምህሩ መማሪያ፣ ለማና ዘመዶቹ፣ ለማ በትምህርት ቤት፣ ለማ በገበያ ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም በ፲፱፴፰ ዓ.ም. ያሳተሙት የአማርኛ ንግግር መሣሪያ ለመምህሩ መምሪያ ይገኝበታል፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
|
ገብሬ በ፲፱፲፱ ዓ.ም. በመንዝና ግሼ አውራጃ ማማ ምድር ወረዳ እምቢ ጣጣ ቀበሌ ተወለዱ፡፡ ከተወለዱበት አካባቢ በ፲፱፴፫ ዓ.ም. ለቀው አዲስ አበባ መጡ፡፡ መጀመሪያ በዓታ ከዚያም ዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት ገብተው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። |
|
|
|
|
|
አባ ገብረ ክርስቶስ |
|
|
|
|
|
አለቃ ገብረአብ |
|
|
|
|
|
ገሪማ ተፈሪ |
|
|
|
|
|
ገብረወልድ እንግዳወርቅ |
|
|
|
|
|
ገነት አየለ |
|
|
|
|
|
ገብረ ጊዮርጊስ ትርፌ |
|
|
|
|
|
አዛዥ ጌራና አዛዥ ራጉኤል |
|
|
|
|
|
መጋቤ ምስጢር ጌራወርቅ ጥበቡ |
|
|
|
|
|
ጌታሁን አማረ |
|
|
|
|
|
ጌታቸው የሮም |
|
|
|
|
|
ጌታቸው በለጠ |
|
|
|
|
|
ጌታቸው ወልዩ |
|
|
|
|
|
መሪ ጌታ ግርማጽዮን መብራህቱ |
መሪጌታ ግርማጽዮን መብራህቱ በ፲፱፲፰ ዓ.ም. ኤርትራ ውስጥ ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢያቸው የቤተክርስቲያን ትምህርት እየተማሩ አደጉ፡፡ በየገዳማቱ እየተዘዋወሩ ጸዋት ወዜማ ተማሩ። ወደ ጎንደር ተጉዘውም የዜማና የአቋቋም ትምህርት አጠናቅቀው በመመረቅ ወደ ትውልድ ቀበሌያቸው በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመሪ ጌታነት እያገለገሉ ብራና ፍቀው ቆርጠውና ቀለም በጥብጠው ብዙ የብራና መጽሐፍትን ጽፈዋል፡፡
መሪጌታ ግርማጽዮን በቤተክርስቲያን ትምህርት ሙሉ ዕውቀት ያላቸው ከመሆኑም በላይ በዘመናዊ ትምህርት እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ድረስ ተምረዋል፡፡ በወሎ ክፍለ ሀገር ይሰጥ በነበረው የመምህራን ሥልጠና ተካፍለው በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ ለመማሪያነት የሚያገለግሉ የተለያዩ የአማርኛ መጽሐፍትም አዘጋጅተዋል፡፡ ቀደም ሲልም “የሃይማኖት ጋሻ ለጠላት መመለሻ” በሚል ርዕስ ስለኢትዮጵያ አንድነትና ስለ ሕዝቧ ጀግንነት የሚያወሳ መጽሐፍ ደርሰው አሳትመዋል፡፡ መሪጌታ ግርማጽዮን ታላቁንና የመጀመሪያውን የትግርኛ መዝገበ ቃላት ሲያዘጋጁ ያልዳሰሱት አውራጃ፣ ያላገላበጡት መረጃ አይገኝም፡፡ በስድስት መቶ ሃምሳ ገላጭ ሥዕሎች የተዘጋጀው “የትግርኛ መዝገበ ቃላት” ለትግርኛ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማበርከቱም በላይ ለማስተማሪያነትም ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡
ይህም ዐብይ ሥራቸው በሀገራችን የሥነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛውን ቦታ የሚይዝ ነው፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
|
መሪጌታ ግርማጽዮን መብራህቱ በ፲፱፲፰ ዓ.ም. ኤርትራ ውስጥ ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢያቸው የቤተክርስቲያን ትምህርት እየተማሩ አደጉ፡፡ በየገዳማቱ እየተዘዋወሩ ጸዋት ወዜማ ተማሩ። |
|
|
|
|
|
ግርማ ታደሰ |
|
|
|
|