[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
የኢትዮጵያ ደራሲያን በፊደል ማውጫ
አ
በ
ቨ
ገ
ደ
ጀ
ሀ
ወ
ዘ
ዠ
ሐ
ኀ
ጠ
ጨ
የ
ከ
ኸ
ለ
መ
ነ
ኘ
ሠ
ዐ
ፈ
ጸ
ፀ
ቀ
ረ
ሰ
ሸ
ተ
ቸ
ጰ
ፐ
ወደ ዋና ገጽ
ተስፋዬ አለነ አባተ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
[1906 - 1992]
ተክለጻድቅ መኩሪያ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተክለጻድቅ: መኩሪያ: ባ፲፱፻፮: ዓ.ም. : በተጉለትና: ቡልጋ: አውራጃ: አሳግርት: ልዩ: ስሙ: ሣር: አምባ: በተባለ: ሥፍራ: ተወለዱ።
ዕድሜያቸው: ለትምህርት: ሲደርስ: መዠመሪያ: ካ’ባታቸውና: ቀጥሎም: ባ’ጥቢያቸው: ባህላዊውን: ትምህርት: እስከ: ቅኔ: ያለውን: ቀስመዋል።
ከዚያም: ዐዲስ: አበባ: መጥተው: አሊያንስ: ፍራንሴዝና: ከተፈሪ: መኮንን: ት/ቤት: ገብተው: የጊዜውን: የትምህርት: ደረጃ: አጠናቀቅዋል።
ኢጣሊያ: አገራችንን: የወረረች: ጊዜም: በየካቲት: ፲፪: ቀን: ፲፱፻፳፱: ዓ.ም.: ፍጅት: ተይዘው: ወደ: ሶማሊያ: ደናኔ: ተግዘው: ለሦስት: ዓመታት: ታሥረዋል።
ከነጻነትም: መልስ: አገራቸውን: በተለያዩ: የኃላፊነት: ደረጃዎች: አገልግለዋል። መዠመሪያ: ተቀጥረው: ያገለገሉት: በትምህርትና: ሥነጥበብ: ሚኒስቴር: ነበር። እዚያም: እያሉ: ባነራችን: ሰው: የተጻፈ: የአገራችን: ታሪክ: አንድም: ባለመኖሩ: በቁጭትና: በመቆርቆር: ነበር: ‘መጻፍ: አለብኝ’: ብለው: በደንብ: ከሚታወቀው: ከቅርቡ: ጊዜ: በቅጡ: ወደማይታወቀው: የሩቁ: ዘመን: መጣፍ: የዠመሩት።: የመዠመሪያውን: መጽሐፍ: “የኢትዮጵያ: ታሪክ: ከዐፄ: ቴዎድሮስ: እስከ: ቀ.ኃ.ሥ.”: ባ፲፱፻፴፰: ዓ.ም.: አሳተሙ። ከጫፍ: እስከጫፍ: ጽፈው: የመጨረሻውን: መጣፍ: የታሪካችን: መዠመሪያ: የሚኾነውን: የኢትዮጵየ: ታሪክ: ኑብያ - አክሱም - ዛጉዬ: እስከ: ዐፄ: ይኩኖ: አምላክ: ዘመነ - መንግሥት: የሚለውን: ባ፱፻፶፩: ዓ.ም.: አቅርበዋል። እንህኑ: መጻሕፍት: ትምህርት: ሚኒስቴር: ታሪክ: ለማስተማሪያ: በትምህርት: ቤት: ተጠቅሞባቸዋል።
ተክለጻድቅ: ከታሪክ: ውጭ: የጻፉዋቸው: “የሰው: ጠባይና: ዐብሮ: የመኖር: ዘዴና: በሚዮቶሎዢያ: ላይ: ያተኮረ: ከጣዖት: አምልኮ: እስከ: ክርስትና”: የሚሉም: መጣፎች: አሏቸው።
ተክለተድቅ: በምድር: ባቡር: በዋና: ጸሐፊነት: በቤተመጽሐፍት: ወመዘክር: ዋና: ሥራ: አስኪያጅነት፤ እንዲሁም: በፈረንሣይ፣ በእስራኤል፣ በዩጎዝላቪያ: በዲፕሎማሲ: ሥራ: በመጨረሻም: የትምህርትና: የባህል: ሚኒስትር: ኾነው: አግልግለዋል። በፈቃዳቸው: ጡረታ: ከወጡም: በኋላ: በምርምር: የታገኑ: ሦስት: ታላላቅ: የታሪክ: ሥራዎችን: አቅርበዋል።
ተክለጻድቅ: ከረዥም: ያገልግሎት: ዘመን: በኋላ: በተወለዱ: በ፹፮: ዓመታቸው: ሐምሌ: ፲፮ቀን: ባ፲፱፻፺፪: ዓ.ም.: ዐርፈዋል።
ምንጭ:
ያሠርቱ: ምእት ፥ የብርእ: ምርት: ከ፲፻: እስከ: ፳፻: ድርሰት: ክፍል: ፩
ዻጉሜ: ፫: ቀን: ፲፱፻፺፱: ዓ.ም: በብርሃነመስቀል: ደጀኔ እና ጌታሁን: ሽብሩ።
ተክለጻድቅ: መኩሪያ: ባ፲፱፻፮: ዓ.ም. : በተጉለትና: ቡልጋ: አውራጃ: አሳግርት: ልዩ: ስሙ: ሣር: አምባ: በተባለ: ሥፍራ: ተወለዱ።
ተድላ ዘዮሐንስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
አዛዥ ተክለሥላሴ ጢኖ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ አበበ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተሻለ አሰፋ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ መኮንን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ መኮንን ባይለየኝ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተፈራ ደግፌ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተሰማ ታኣና አሌሳንድሮ ትሪዩልዚ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ ሀብተማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ ገ/ማርያም ኃይሉ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ ገ/ማርያም ነሐሴ ፩፮ ቀን ፲፱፵፪ ዓ.ም. በቀድሞ ወለጋ ክ/ሀገር ጊንቢ አውራጃ ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አሶሳ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ነቀምት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በሐረር መምህራን ማሠልጠኛና በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡ ተስፋዬ ገ/ማርያም ቁጥራቸው የበዙ መተሕፍትን ለአንባብያን አበርክተዋል፡፡
ካበረከቷቸው መጻሕፍት መካከል “የግችሌ ሜዳ”፣ “በድሉ በረኛው”፣ “አደን ደኀና ሰንብት”፣ “ሽሽጉ ቀነኒ”፣ “እኮ ማን ያስከብራል”፣ “ቾምቤና ወፎቹ”፣ “ሽታዬ” እና ሌሎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ተስፋዬ ገ/ማርያም ነሐሴ ፩፮ ቀን ፲፱፵፪ ዓ.ም. በቀድሞ ወለጋ ክ/ሀገር ጊንቢ አውራጃ ተወለዱ።
ተስፋዬ ገሰሰ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተስፋዬ ሐረርጌ ውስጥ ልዩ ስሙ ጎሮ ጉቱ በሚባል አካባቢ በ፲፱፳፱ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በልጅነታቸው ወላጆቻቸው በሞት ስለተለዩዋቸው አዲስ አበባ ዘመድ ቤት በመቀመጥ ትምህርታቸውን ተከታተሉ፡፡ የተፈሪ መኮንን ተማሪ በነበሩበት ወቅት ብዙ መጻሕፍት ከማንበብ ይልቅ እግር ኳስና ሌሎች ጨዋታዎችን ያዘወትሩ ነበር። በተለይ ግን የከበደ ሚካኤልን "የትንቢት ቀጠሮ" ተውኔት ይወዱ እንደነበር ይናገራሉ፡፡
በ፲፱፵፰ ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ገቡ፡፡ የፊልም ወይም የመድረክ ተዋናይ የመሆን ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም አጠቃላይ ጥበብ ጄኔራል አርትስ ሜጀር አድርገው የሕግ ትምህርት አጠኑ፡፡
የዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመረቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ሄደው ለሁለት ዓመታት ቆይተዋል፡፡
"የቴያትር ጥበብን በማጥናት በኢትዮጵያ ያለውን የቴያትር ባህል ለማሳደግ" በቆራጥነት የተነሱት አሜሪካ እያሉ ነበር፡፡ ቴያትር እንዲያጠኑ ሐሳቡን የጫሩባቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴያትር ባሳዩበት ወቅት በአተዋወን ብቃታቸው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተደስተው ሰዓት በመሸለም "ቴያትር" እንዲያጠኑ ከነገሯቸው በኋላ ነው፡፡
ከአሜሪካ በ፲፱፶፬ ዓ.ም. ከተመለሱ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ቴያትር ቤት በመቀጠር የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ሥራ የሆነውን "የሾህ አክሊል"ን በማዘጋጀትና የዋና ገፀባህሪውን በመወከል ተውነዋል፡፡ "የሺ" የሚል ተውኔት በመጻፍም ለመድረክ አብቅተዋል፡፡ በ፲፱፶፫ ዓ.ም. በእንግሊዝኛ ቋንቋ "ላቀችና ማሰሮዋ" የሚል ተውኔት ደርሰዋል፡፡
በርካታ ተውኔቶች ላይ የትወና ችሎታቸውን ያስመሰከሩ አጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞቻቸው በሩሲያኛ ተተርጉመው ሩሲያ ውስጥ ታትመዋል፡፡ የኡመር ካየምን መጽሐፍ "ሩብ አያት" በማለት ተርጉመው አሳትመዋል፡፡ በተጨማሪም በ፲፱፷፭ ዓ.ም. መተከዣ የሚል መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ተስፋዬ ሐረርጌ ውስጥ ልዩ ስሙ ጎሮ ጉቱ በሚባል አካባቢ በ፲፱፳፱ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በልጅነታቸው ወላጆቻቸው በሞት ስለተለዩዋቸው አዲስ አበባ ዘመድ ቤት በመቀመጥ ትምህርታቸውን ተከታተሉ፡፡ የተፈሪ መኮንን ተማሪ በነበሩበት ወቅት ብዙ መጻሕፍት ከማንበብ ይልቅ እግር ኳስና ሌሎች ጨዋታዎችን ያዘወትሩ ነበር።
[1902 - 1943]
ተመስገን ገብሬ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ተመስገን ገብሬ የተወለዱት በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረማርቆስ ከተማ በ1902 ዓ.ም. ነው፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተ ክህነት ትምህርት ተከታትለዋል፡፡ ቤተሰባቸው ካህናት ከመሆናቸውም በላይ ጎበዝ ተማሪ ነበሩ። ጉብዝናቸው በዘመናዊ ትምህርት ሲከታተሉም ጎልቶ ወጥቷል፡፡ ከጎጃም አዲስ አበባም በመምጣት በሲውዲን ሚሽን ትምህርት ቤት ተማሩ በወቅቱ ሀገሪቱ ካፈራቻቸው ጎበዝ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ፡፡
ተመስገን በጋዜጠኝነት ሙያ ከመስራታቸውም በላይ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በኃላፊነት ቦታ ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በጣሊያን በተወረረችበት ወቅት በዐርበኝነት ከጠላት ጋር ተፋልመዋል፡፡ ሱዳን ተሰደው ገዳሪፍ ውስጥ እያሉ ኢትዮጵያዊያንን በልዩ ልዩ መልክ አስተምረዋል፡፡ ጣሊያን ከለቀቀች በኋላ የዘመናዊ አስተሳሰብና ዕድገት ዓላማዋ ዕውን እንዲሆን ፍፁም የለውጥ ዐርበኛ ሆነው ሠርተዋል፡፡
ተመስገን “የጉለሌ ሰካራም” በሚል አጭር ልብወለዳቸው የመጀመሪያ የአገራችን አጭር ልብወለድ ጸሐፊ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ የጉለሌው ሰካራም ከመታተሙ በፊት “የካቲት 12” እና “አለቃ እውነቱ” የተሰኙ ሁለት አጫጭር ልብወለዶችን በጋዜጣ ላይ አውጥተዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ተመስገን ገብሬ የተወለዱት በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በደብረማርቆስ ከተማ በ1902 ዓ.ም. ነው፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተ ክህነት ትምህርት ተከታትለዋል፡፡ ቤተሰባቸው ካህናት ከመሆናቸውም በላይ ጎበዝ ተማሪ ነበሩ።
ታረቀኝ ጎጄ] ዓለሙ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታዬ ገብረማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደሰ ሊበን
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
በጻፏቸው አጫጭር ልብ ወለዶች የሚታወቁት ታደሰ ሊበን በ፲፱፳፫ ዓ.ም. ወለጋ ውስጥ ደንቢዶሎ ተወለዱ። ገና የስድስት ዓመት ልጅ እያሉ አባታቸው ሞተውባቸዋል። እናታቸው ጥሩ ጥሩ ተረቶች እየተረኩላቸው ያደጉት ታደሰ ሊበን የልብወለድ ፍቅር ያደረባቸው በዚያን ጊዜ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡
ከመንግሥቱ ለማ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ ነገር ግን በ፲፱፵፱ ዓ.ም. “መስከረም” እና በ፲፱፶፪ ዓ.ም. “ሌላው መንገድ” በሚል ርዕስ የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ ካሳተሙ በኋላ ሌላ መጽሐፍ ባለማሳተማቸው ከመንግሥቱ ለማ ጋር ተቀያይመዋል፡፡
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የአጭር ልብወለድ የመጀመሪያው ጸሐፊ በመባል ይታወቁ ነበር፡፡ ነገር ግን “የጉለሌው ሰካራም” ጸሐፊ ተመስገን ገብሬ የመጀመሪያው የአጭር ልብወለድ ጸሐፊ መሆናቸው ከታወቀ በኋላ ቀድሞ የነበረው አስተሳሰብ ቢቀየርም በሥነ ጽሑፍ እድገት ላይ ያደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ግን የሚዘነጋ አይደለም፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
በጻፏቸው አጫጭር ልብ ወለዶች የሚታወቁት ታደሰ ሊበን በ፲፱፳፫ ዓ.ም. ወለጋ ውስጥ ደንቢዶሎ ተወለዱ።
ታዬ ገብረ ማርያም
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደሰ ሜጫ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታምራት ይገዙ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታቦር ዋሚ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታክሎ ተሾመ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደለ ብጡል ክብረት
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደለ ብጡል ኢንጂነር ታኀሣሥ ፩ ቀን ፲፱፳ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀ.ኃ.ሥ. ኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርታቸውን በተባበሩት አሜሪካ በ”ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዊስ ካንሰንና ቺካጎ” የተከታተሉ ሲሆን በስዊድን ስቶክሆልም ስትራክቸራል ዲዛይን ሲሆን፤ የሲቪል ምሕንድስና ባለሙያም ናቸው፡፡
ታደለ ብጡል “ማራዠት” በሚል ርዕስ የግጥም መድብል አንደኛ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ በተጨማሪም “ሦስትዮሽ” የግጥም መድብል፣ እንዲሁም “ውይይት” በሚል ርዕስ ሌሎች ሥራዎችንና ወጎችን ከክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ጋር አቅርበዋል፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ታደለ ብጡል ኢንጂነር ታኀሣሥ ፩ ቀን ፲፱፳ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለዱ።
ታደለ ገብረሕይወት
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ታደለ ገ/ሕይወት ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፲፱፴፰ ዓ.ም. በግዮን አምቦ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞው ቀ.ኃ.ሥ. ኮከበ ጽባሕ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ተምረው በፖለቲካል ሳይንስና ሥነ-መንግሥት ትምህርት በዲፕሎማ ተመርቀዋል።
ታደለ ገ/ሕይወት “ማነው ኢትዮጵያዊ?”፣ “ኢትዮጵያ ትቅደም”፣ “ከርሞ ዘማች” “ተራማጅ ጥቅሶች”፣ “ለቀዩ አበባ”፣ “ብቀላ” የተሰኙ የፈጠራና የትርጉም ሥራዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡
ምንጭ:
የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
ታደለ ገ/ሕይወት ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፲፱፴፰ ዓ.ም. በግዮን አምቦ ተወለዱ፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞው ቀ.ኃ.ሥ. ኮከበ ጽባሕ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ተምረው በፖለቲካል ሳይንስና ሥነ-መንግሥት ትምህርት በዲፕሎማ ተመርቀዋል።
አቡነ ቴዎፍሎስ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
ትኩእ ባህታ
የደራሲውን ሥራዎች ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ።
መጻሕፍት ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ
ይጫኑ
ተመዝግበው ከሆነ እዚህ
ይጫኑ
[
ታሪክ
|
ምርምርና ጥናት
|
ልቦለድ
|
ግጥምና ቅኔ
|
ተውኔት
|
ትምህርት
|
ፍልስፍና
|
ተረቶችና ቀልዶች
|
ትርጉም
|
ቋንቋ
|
ወግ
|
መንፈሳዊ ድርሰቶች
|
መዛግብተ-ቃላት
]
[
ዋና ገጽ
|
ስለኛ
|
አስተያየት
|
አድራሻችን
]
መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com