|
|
በሪሁን ከበደ |
|
|
|
|
|
በቀለ ተገኝ |
|
|
|
|
|
በቀለ ሰጉ |
|
|
|
|
|
በረከት ስምኦን |
|
|
|
|
|
በድሉ ዋቅጅራ |
|
|
|
|
|
በእምነት ገብረአምላክ |
በእምነት የተወለዱት በ፲፱፲፫ ዓ.ም. ነበር፡፡ በኤርትራ ገጠራማ አካባቢ የተወለዱት በእምነት ከቤተሰቦቻቸው ጋር አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በስዊድን የሚሲዮን ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን መከታተል ቢጀምሩም በጣሊያን ወረራ ምክንያት ለማቋረጥ ተገደዋል፡፡ ቀጥሎም ጣሊያን ኮንስላታ ትምህርት ቤት በመግባት ትምህርታቸውን ቀጥለው በቤተሰብ ችግር ምክንያት አቋርጠዋል፡፡ ለጣሊያኖች በፎቶግራፍ አንሺነት ተቀጥረው ሰርተዋል፡፡ የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ በኃይል ተሸንፎ ከተባረረ በኋላ በፖሊስ ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት ለስድስት ዓመታት አገልግዋል፡፡ ወደ አሜሪካ በመሄድ ትምህርት መማር ቢጀምሩም በአየር አለመስማማት ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል በ፲፱፶፰ ዓ.ም. በቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ በማዕረግ ተመረቁ፡፡ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የማስተማር ዕድል አጋጥሟቸው በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ለመሥራት አሜሪካ የሄዱ ቢሆንም ነገር ግን የቤተሰብ ችግር ስላጋጠማቸው ትምህርታቸውን ሳይጨርሱ ለመመለስ ተገደዋል፡፡
ለአማርኛ ቋንቋ ማደግ ይከራከሩ የነበሩት በእምነት የተለያዩ የትርጉም ሥራዎች ቢኖሯቸውም በእጅጉ የሚታወቁት ግን “ልጅነት ተመልሶ አይመጣም” በሚለው ተወዳጅ ድርሰታቸው ነው፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ ካሌንደር። |
በእምነት የተወለዱት በ፲፱፲፫ ዓ.ም. ነበር፡፡ በኤርትራ ገጠራማ አካባቢ የተወለዱት በእምነት ከቤተሰቦቻቸው ጋር አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። |
|
|
|
|
|
ባይሩ ታፍላ |
|
|
|
|
|
ባቢሌ ቶላ |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ አስረስ |
|
|
|
|
|
[1925 - 1979] |
|
ብርሃኑ ዘርይሁን |
ብርሃኑ ዘርይሁን በ1925 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተክርስትያን ትምህርት ተምረዋል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጎንደር ይገኝ በነበረው በቀድሞው ቀዳማዊ ሃይለሥላሴ ትምህርትቤት አጠናቀቁ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥተው በተግባረ እድ ትምህርት ቤት በሬዲዮ ቴክኒሺያንነት ሙያ ተመረቁ።
ሥራ የጀመሩትም በመምህርነት ነው። በወቅቱ በካርታ ሥራ ድርጅት ቴክኒሺያንነት ሙያ ሠርተዋል። ከዚያም የጦር ሚኒስቴር እየተባለ ይጠራ በነበረው የአሁኑ መከላከያ ሚኒስትር በአስተርጓሚነት አገልግሏል። ማስታወቂያ ሚኒስትር እንዲዛወሩ ከተደረገ በኋላ የኢትጵያ ድምጽ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆነዋል። ከሶስት አመት በኋላ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆነው የማይረሳ ተግባር አከናውነዋል።
ብርሃኑ ዘርይሁን የደረሱት ‹ሞረሽ› በ1972 ዓ.ም፤ ‹ጣጠኛው ተዋናይ›በ1975 ዓ.ም እና ‹አባደፋር› በ1977 ዓ.ም፤ የተባሉት ቴያትሮቻቸው ተወዳጅ ነበሩ።
ከጻፏቸው መጻሕፍት ውስጥም ‹የቴዎድሮሥ እንባ › በ1958 ዓ.ም፤ ‹የእንባ ደብዳቤዎች› በ1961 ዓ.ም እና የታንጉት ምሥጢር› በ1978 ዓ.ም፤ እንዲሁም ለረጅም ተከታታይ ጊዜያት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ሲተረኩ የነበሩት ‹የአብዮት ዋዜማ፤የአብት መባቻና የአብዮት ማግስት› የተሰኙት ማጸሐፍት ይገኙበታለል።
ብርሃኑ ዘርይሁን ለሐገራቸው የስነ ጽሁፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዎ አበርክተዋል። በቀዳሚዎቹ ዘመናት የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበርን በሥራ አመራር አባልነት ካገለገሉት መካከል አንዱ ብርሃኑ ናቸው።
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |
ብርሃኑ ዘርይሁን በ1925 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የቤተክርስትያን ትምህርት ተምረዋል፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጎንደር ይገኝ በነበረው በቀድሞው ቀዳማዊ ሃይለሥላሴ ትምህርትቤት አጠናቀቁ፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ መጥተው በተግባረ እድ ትምህርት ቤት በሬዲዮ ቴክኒሺያንነት ሙያ ተመረቁ። |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ አበበ |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ ለሜሳ |
|
|
|
|
|
ብስራት አማረ |
|
|
|
|
|
ብርሃኑ ነጋ |
|
|
|
|