ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ማሞ ውድነህ
[1928 - 2004]
የደራሲው ሥራዎች
1.   አሉላ አባ ነጋ(ታሪክ)
2.   አሉላ አባነጋ(ተውኔት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ማሞ ውድነህ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. በቀድሞ አጠራር በወሎ ክፍለ ሀገር በዋግ አውራጃ በዳህና ወረዳ አምደወርቅ ከተማ ተወለዱ፡፡ በቤተክህነት ትምህርት ዳዊት እስከመድገም ደርሰዋል፡፡ ከ፲፱፵ ዓ.ም. ጀምሮ በደሴ በንጉሥ ሚካኤል ትምህርት ቤት የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ትምህርት ቤቶች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተምረዋል፡፡

በመጀመሪያ በመምህርነት ቀጥሎም በውጭ ሀገር ኤምባሲዎች ሠርተዋል፡፡ በማስታወቂያ ሚኒስቴር በፖሊስ ሠራዊትና በቀድሞ ኤርትራ ክፍለ ሀገር በፕሬስ የሥራ ክፍሎች ውስጥ ሠርተዋል፡፡ ከ፲፱፹፭ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ፲፱፺፯ ዓ.ም. ድረስ የደራስያን ማህበርን በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል፡፡ ልብ ወለድ፣ አጫጭር ድርሰት፣ ግጥምና ቅኔ፣ የቲያትር መጻሕፍትን በመድረስና በመተርጎም ይታወቃሉ፡፡ ካሳተሟቸው 5ዐ ያህል መጻሕፍት መካከል ሁለተኛው የዓለም ጦርነት፣ የሴቷን ፈተና፣ ከወንጀለኞች አንዱ፣ ቬኒት ሙሶሎኒ፣ ዘጠና ደቂቃ በኢንተቤ እና ዕቁብተኞቹ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡም "የደረስኩበት" በሚል ርዕስ ግለ ታሪካቸውን የተመለከተ 5ዐኛው መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጽ አሳትመዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com