በላይ ግደይ በቀድሞው ትግራይ ክ/ሀገር መጋቢት 7 ቀን በ1920 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ በተወለዱበት ሥፍራ ፊደል ከቆጠሩ በኋላ በ1937 ዓ.ም. አ.አ. ዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት ገብተው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተማሩ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞው ንግድ ሥራ ትምህርት ቤት አጠናቀዋል፡፡ በተጨማሪም በአ.አ. ዩኒቨርሲቲ በማታው የትምህርት መርሐ ግብር የከፍተኛ ትምህርት የተከታተሉ ሲሆን በውጭ ሀገርም የባንክ አገልግሎት ሥራ ተምረዋል፡፡
በላይ ግደይ “ገንዘብ፣ ባንክና መድን በኢትዮጵያ”፣ “የኢትዮጵያ ሥልጣኔ”፣ “ቅድስት አክሱም”፣ በሚሉ ርዕሶች መጽሐፎችን በአማርኛ ቋንቋ አዘጋጅተውና አሳትመው ለአንባብያን ያቀረቡ ሲሆን፣ “Currency ad Banking in Ethiopia”፣ “Ethiopian Civilization” በሚሉ ርዕሶችም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ጽፈው ያዘጋጇቸውና ያሳተሙዋቸው መጻሕፍትም አሏቸው፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
|