አቶ አሰፋ ገ/ማርያም ተሰማ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርበኞች ት/ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጄኔራል ውንጌት ት/ቤት ተምረዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በቀድሞው ሶቪየት ኀብረት ሌኒን ግራድ ዩኒቨርሲቲና በእንግሊዝ ሀገር በሚገኘው ኢንደንብራ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ሰልጥነዋል፡፡
ለኀትመት የበቁላቸው ሥራዎች "የመስከረም ጮራ"፤ እና “The Voice” የተሰኙ የግጥም መድብሎች ይጠቀሳሉ፡፡ በቲአትር ዘርፍ "ዩሊየስ ቄሳር"፣ "ዋናው ተቆጣጣሪ" የትርጉም ሥራዎች እና "ከለንደን አዲስ አበባ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ወጥ ቲአትር ለመድረክ አብቅተዋል፡፡ የደርግ ዘመንን ብሔራዊ የሕዝብ መዝሙርም ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኀበርን በዋና ፀሐፊነት መርተዋል፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
|