ብርሃኔ ጉቻለወርቅ በሸዋ ክፍለ ሀገር ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በ፲፱፳፪ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት በደረሰ ጊዜም ትምህርታቸውን በማታው ክፍለ ጊዜ በመከታተል ከየንግድ ሥራ ትምህርት ቤት የምስክር ወረቀት አግኝተዋል።
ብርሃኔ ጉቻለወርቅ ጥቅምት ፲፱፳፫ ዓ.ም. በወታደርነት ተቀጥረው ለአሥር ዓመታት፤ በሲቪል ፀሐፊነት ደግሞ ለሃያ ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከ፲፱፶፫ ዓ.ም. ጀምሮ ድርሰት መጻፍ የጀመሩት ብርሃኔ ጉቻለወርቅ ከጻፏቸው መጻሕፍት መካከል “ፈላስፋው ቃየል ነው”፣ “እሬትና ማር”፣ “የድሆች ጠበቃ”፣ “ዳኞች በፍርድ ላይ”፣ “ባሌ መታኝ አለች ወይስ ፈታኝ” የሚባሉት የገኙበታል፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |