ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ተባባሪ ፕሮፌሰር አቦነህ አሻግሬ
የደራሲው ሥራዎች
1.   ኩረባ(ተውኔት)

ስለደራሲው በጥቂቱ
አቦነህ አሻግሬ ተባባሪ ፕሮፌሰር በቀድሞው ኢሉባቡር ክ/ሀገር ጎሬ ከተማ መጋቢት ፭ ቀን ፲፱፵፫ ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከ፲፱፶-፲፱፩ ዓ.ም. ድረስ ጎሬ ኢሊባቡር፣ ጋምቤላና አዲስ አበባ 10 2፣ ኮተቤ መምህራን ማሠልጠኛ ት/ቤት ገብተው በመምህርነት ሙያ ትምርታቸውን አጠናቀዋል። ከአ.አ. ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ክፍል በቴአትር ጥበብ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፣ ከአሜሪካ ኦሀዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከቴአትር ጥበባት ክፍል የማስተርስ ዲግሪያቸውን ወስደዋል፡፡

አቦነህ አሻግሬ “ቅኝት”፣ “ባሕር ማዶ”፣ የተሰኙ ቴአትሮቻቸውን በብሔራዊ ቴአትርና በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት አሳይተዋል፡፡ “ኩኩ መለኮቴ”፣ “አባ ጉጉ”፣ “የሰማዩ ሰረገላ”፣ በመባል የሚታወቁ የሕጻናት ቴአትሮቻቸው፣ በአዲስ አበባ የሕጻናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት፣ ሜጋ አምፊ ቴአትር ለሕዝብ ታይተዋል፡፡ ለአዋቂዎች ያዘጋጇቸው “ሊቀማዕምር” “ኩረባ”፣ የተባሉ ተውኔቶቻቸውም እንዲሁ ለመድረክ በቅተዋል፡፡ “እንቁጢ እንቁጣጣሽና ሌሎች ልቦለዶች”፣ በሚል መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com