ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ዶ/ር ላጵሶ ጌ.ድሌቦ
የደራሲው ሥራዎች
1.   የኢትዮጵያ ረጅም የሕዝብና የመንግሥት ታሪክ(ታሪክ)
2.   የኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ መሰረቶችና መሳሪያዎች(ታሪክ)
3.   የኢትዮጵያ የገባር ሥርአትና ጅምር ካፒታሊዝም(ታሪክ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ላጲሶ ጌታሁን ድሌቦ ፕሮፌሰር በከንባታና ሐዲያ አውራጃ በኩፋላ ሐበሌ ግንቦት ፲፪ ቀን ፲፱፻፴ ዓ.ም. ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቢቾ ሆሣዕና ሚሽን ት/ቤትና በመንግሥት ትምህርት ቤት ሲከታተሉ ቆይተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዓጼ ገላውዴዎስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በባይብል አካዳሚ ናዝሬት ተምረዋል፡፡ ከዚያም በአሜሪካ ኮሙኒቲ ኮሌጅ የከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለው በኀብረተሰብ ታሪክ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ ከሐዋርድ ዩኒቨርሲቲም በአፍሪካ ታሪክ ጥናት የኤም.ኤ ዲግሪያቸውን፣ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካና በአውሮፖ ታሪክና በፍልስፍና የፒ.ኤች.ዲ ዲግሪያቸውን ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ ወስደዋል፡፡

ላጵሶ ጌታ ድሌቦ “የኢትዮጵያ የገባር ሥርዓትና ጅምር ካፒታሊዝም፣ 1ኛና 2ኛ የታሪክ መጻሕፍት”፣ “የኢትዮጵያ ረጅም የሕዝብና የመንግሥት ታሪክ 1ኛ መጽሐፍ”፣ “የቀይ ባሕርና የአባይ ሸለቆ ሚና፣ የምፅዋ ሲምፖሲየም-1974”፣ “የኢትዮጵያ የመከራ ሥርዓትና የኤርትራ ጥያቄ፣ 1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ መጽሐፍ” ና ሌሎች በርካታ የታሪክ መጻሕፍት አሳትመው ለአንባብያን አቅርበዋል፡፡

ምንጭ: የኢትዮጵያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com