ወንድሙ ነጋሽ ደስታ መስከረም ፲፮ ቀን ፲፱፴፰ ዓ.ም. በጅማ ከተማ ተወለዱ። የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞጆ ሚያዝያ 27 ት/ቤት ጅማ፣ የሁለተኛ ደረጃን በኮከበ ጽባሕ አዲስ አበባ ተከታትለዋል፡፡ ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ ክፍል፣ በሥነ- ጽሑፍ ተመርቀዋል፡፡
ወንድሙ ነጋሽ ደስታ “ከሼክስፒር ሥራዎች” “ፍጻሜው ሲያምር”፣ እና “ወዳጅ ሲከዳ”፣ በመባል የሚታወቁትን የሼክስፒር ሥራዎችን ተርጉመው አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም “እንቡጥ ጽጌረዳ” በተሰኘው ረዥም ልቦለድ ሥራቸው ይታወቃሉ፡፡
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ። |