በመርሐቤቴ ረመሸት ቀበሌ ደን አቦ በሚባል አካባቢ የተወለዱት ኀሩይ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያሳዩት በነበረው ትጋትና ቅልጥፍና ፀሐፌ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ ቀድሞ ይጠሩበት የነበረውን ገብረመስቀልን በመቀየር ኀሩይ አሏቸው።
ለዓፄ ኃይለሥላሴ የቅርብ አማካሪ በመሆን የሃይማኖትና የአስተዳደር ሕጎች እየተረጎሙና የአርትኦት ሥራዎቻቸውን እያጠናቀቁ እንዲወጡ ያደረጉት ብላቴን ጌታ ኀሩይ ታሪክ፣ ማኀበራዊ ጉዳይንና ፍልስፍናን ያካተቱ 42 የሚደርሱ መጻሕፍትን አሳትመዋል፡፡ ከሥራዎቻቸው መካከል “ወዳጄ ልቤ” የሚባለው መጽሐፍ ታዋቂነትንና ተወዳጅነትን አትርፎላቸዋል።
ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን መሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው ካሌንደር። |