ደራሲያን በፊደል ማውጫ
   
 
 
ዳኛቸው ወርቁ
[1928 - 1987]
የደራሲው ሥራዎች
1.   እምቧ በሉ ሰዎች(ግጥምና ቅኔ)
2.   ሰው አለ ብዬ(ተውኔት)
3.   ያላቻ ጋብቻ ፥ትርፉ ሐዘን ብቻ(ተውኔት)
4.   Shout It From the Mountain Top ያልታተመ(ልብወለድ)

ስለደራሲው በጥቂቱ
ዳኛቸው ወርቁ በ፲፱፳፰ ዓ.ም. ደብረሲና ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚያው በደብረሲና አጠናቀቁ:: የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረዋል፡፡ በ፲፱፶፫ ዓ.ም. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውም በማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የተቃውሞ ግጥሞችን ይጽፉ ነበር፡፡ ይህንንም በተመለከተ ስብስብ ሥራዎቻቸውን "እምቧ በሉ ሰዎች" በሚል ርዕስ መጽሐፍ አሳትመዋል።

ዳኛቸው ወርቁ በአዲስ ዘመንና በየዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጦች ላይ ስለተለያዩ ጉዳዮች ይጽፉ ነበር፡፡ የተለያዩ ተውኔቶችን ጽፈዋል፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን እንደምትቀላቀል በሚነገርበት ጊዜ "ያላቻ ጋብቻ ትርፉ ሐዘን ብቻ" የሚል ተውኔት ደርሰዋል፡፡ ከዳኛቸው ሥራዎች መካከል በ፲፱፷፪ ዓ.ም. ለኀትመት የበቃው "አደፍርስ" የተሰኘው መጽሐፋቸው በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያተረፈ ነው፡፡

በጊዜው የነበረውን የመኳንንቱንና የባላባቱን የአኗኑዋር ሁኔታ እንዲሁም ስለ ሃይማኖት በሰፊው ይገልጻል፡፡ "አደፍርስ" የታሪኩ ባለቤት ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመሆን ከአዲስ አበባ ወደ ባላገር በመሄድ በአንድ ላይ ቤት ተከራይተው መኖራቸውን በመተረክ በከተማውና በባላገሩ መካከል ያለውን ከፍተኛ የአስተሳሰብ፣ የልማድና የመሳሰሉትን ልዩነቶች በጉልህ ያሳያል፡፡

ምንጭ: የኢትዮዽያ ደራሲያን ማሀበር ለሚሊኒየም ያሳተመው አጀንዳ።

Reidulf K.Molvaer ዳኛቸው ወርቁን ካነጋገረው በሇላ " Dagnachew Worku: Experimenter and Innovator in Literary Style and Language" በሚል ርእስ የጻፈውን የዳኛቸው ወርቁን ባዮግራፊ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

Dannyachew Worku in "Black Lion" - An Overview By Sebhat G/Egziabher
   
   
       
 
   
     
       

መጸሐፍ ለመዋዋስ መመዝግብ ያስፈልጎታል። ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ

ተመዝግበው ከሆነ እዘህ ይጫኑ
     
 

መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው© 2007 ዓ.ም ethioreaders.com